2009-05-18 14:15:17

የቅድስ አባታችን የሰላምና የሁሉም ሃይማኖትች የጋራው ውይይት ጥሪ



 


ቅዱሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመካከለኛው ምሥራቅ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ክንዋኔው በታሪክና በማኅበረሰብ ልብ ዘንድ ተቀርጾ የሚቀር መሆኑ ተገለጠ። ቅዱስነታቸው በናዝሬት ከተማ ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ተገናኙ። የአይሁድ እልቂት የመታሰቢያ ሥፍራ እንዲሁም የእንባ ግንብ እና ጎልጎታን በቤተልሔም የሚገኘውን የሕክምና ጣቢያ በመጎብኘት ጸልየዋል። በእነዚህ ጉብኝቶች ያሰሙት ንግግር የሰጡት አስተምህሮ እና ያሳዩት ፍቅር የሁሉም ልብ ነክተዋል። RealAudioMP3 ሆኖም ይኽ ሓዋርያዊ ጉብኝት በእስራኤልና በፍልስጥኤም መካከል ባለው አለ መግባባት መሠረት የተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን የተቃውሞ ምልክት ቢያሳዩም ቅሉ፣ ሓዋርያዊ ጉብኝቱ በሕዝቦች መካከል ሰላም፣ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይትን የጠራና አደራ ያለ መሆኑ ተገልጠዋል።

ሁለት ልዑላን አገሮች ተስማምተውና ተግባብተው በሰላም ለመኖር የሚችሉበት ሁኔታ በመፍጠር አሸባሪነትን መግታት፣ የግንብ አጥር በማቆም ሳይሆን በያንዳንዱ ልብ ዘንድ ያለው የጥላቻ አጥር መንቀል ለሰላምና ለመግባባት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በናዚው ጭካኔ ለሞት የተዳረጉት 6 ሚሊዮን አይሁዳውያንን ዘክረው ይኸንን ለመዘከር የሚደረገው የአንድ ድቂቃ የሕሊና ጸሎትና ጸጥታ ተዘክሮ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳዩ አሰቃቂ አደጋ እንዳይከሰት ተስፋ የሚደረግበትም ጭምር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል። እግዚአብሔር ይኽ ክልል አገር ይሆነው ዘንድ የመረጠው በመሆኑ፣ ሁሉም ክርስትያን እስላምና አይሁድ የየራሳቸው የሃይማኖት ታሪክና ባህል መሠረት በማድረግ በዚህ ክልል ስላለው ችግር ግንዛቤ ኑሮአቸው በጋራው መተማመንና መቀባበል ብቻ ሊፈታ እንደሚችል ጠንቅቀው ሊገነዘቡት እንደሚገባ ያነቃቃ ሓዋርያዊ ጉብኝት ነበር።

ስለዚህ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው፣ ካለ መታከት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ሰላምን በመማጠን፣ ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ በማስረዳትም በዚህች ቅድስት መሬት ለሚኖሩት ሁሉ ሰላምን ተመኝተዋል። ክልሉ የስቃይና ልብን በኃዘን የሚነካ ውጥረት የሚታይበት ቢሆንም ቅሉ፣ በእግዚአብሔር የተባረከና የተመረጠ መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ያስገነዘበ ጭምር እንደነበርም ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.