2009-05-18 14:18:09

የሁሉም ሕዝቦች ቀን


ትላንትና በሮማ የሚኖሩት የውጭ አገር ስደተኞች 18ኛው የሁሉም ሕዛብ ቀን አስበው መዋላቸው ተገልጠ። ይህ በሮማ ሰበካ በየዓመቱ የሚካሄደው የሁሉም ሕዝቦች ቀን ሮማ በሚገኘው በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ባሲሊካ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መጀመሩም ታውቀዋል። የሮማ ሰበካ የስክላብሪኒያኒ RealAudioMP3 ማኅበር ከሮማ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ የዘንድሮው የሁሉም ሕዝቦች ቀን፣ ሮማ በሌሎች ሕዝቦች ዐይን በሚል ቃል የተመራ እንደነበርም ተገልጠዋል።

የሮማ ሰበካ የስደተኞች ሓዋርያዊ ኖልዎ ተንከባካቢ ጽ/ቤት ምክትል ሓላፊ ኣባ ፔርፓውሎ ፈሊኮሎ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ “ከተለያዩ አገሮች የተሰባሰቡት እዚህ ሮማ የሚገኙት ስደተኞች በጋራ በማሰባሰብ አብረው እንዲሠሩና በመካከላቸው ግኑኝነት እንዲኖር ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ስደተኛው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ለየራሳቸው መኅበረሰብ ቆሞስ በመሆን የሚያገለግሉት ካህናትና እንዲሁም እዚህ በሮማ ሰበካ የሚያገለግሉት የውጭ አገር ካህናት ጭምር አብረው ቀኑን ሲያስቡ ማየት እጅግ የሚያስደስት ነው። ይህ በዓል እያንዳንዱ የስደተኛው ማኅበረ ክርስትያን ተነጥሎ እንዳይቀር ከሌሎች ስደተኞች ማህበረ ክርስትያን ጋር እንዲተዋወቅ የሚያግዝ፣ ስደተኛ በመሆን የሚያጋጥመው ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊና መንፈሳዊ ችግር በጋራ ለመወጣትና በቤተ ክርስትያን ሓዋርያዊ ኖልዎ አገልግሎት መሠረት በመታገዝም እምነታቸውን በተግባር እንዲኖሩ የሚያነቃቃ ዕለት ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.