2009-05-18 17:52:40

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ጋዜጠኞች፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ መሃከለኛው ምሥራቅ ለአንድ ሳምንት ጐብኝተው ባለፈው ዓርብ በሰላም ወደ መንበረ ሐዋርያቸው እንደተመለሱ የሚታወስ ነው። RealAudioMP3

ቅዱሰነታቸው ከኢየሩሳሌም ወደ ቫቲካን ሲመለሱ ፡ አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩ ጋዜጠኞች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች የመለሱ ሲሆን፡ በሐዋርያዊ ዑደቱ ጋዜጠኞቹ ላከናወኑት ስራ አመስግነው በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ችግር ለመፍታት የሰላም አቢይ እንቅስቃሴ እንደሚያሻ መግለጣቸው ተመልከተዋል።

እስራኤሎችም ሆኑ ፍሊስጢኤማውያን በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም የማስፈን ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰው፡ ፍላጎቱ ገቢራዊ እንዲሆን ማበረታታት ለዕርቅና ለሰላም መቆም እና መስራት እንደሚያስፈልግ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መግለጣቸው ተገልጠዋል።

በዮርዳኖስ እስራኤል እና በፍልስጢኤም ራስ ገዝ ያጋደረጉት ሐዋርያዊ ዑደት፡ የሰላም ዑደት መሆኑ ያመለከቱ ር.ሊ.ቃ. በነዲክቶስ ፡ ዮርዳኖስ ወንዝ ፡ በቅዱስ መቃብር ኢየሱስ ክርስቶስ ፡ቅዱስ ቁርባን በቻረልን ቦታ እና ከሐወርያቱ ጋር ለመጨረሻ እራት የተቀመጠበት በጽርሃ ማርያም ያደረጉት ሐወርያዊ ጉብኝት በእጅጉ እንዳስደሰታቸው ጠቅሰው ፡ ቅዱሳን ቦታዎች የሚጐበኙ ሁሉ የሰላም መልእከተኞች እንዲሆኑ ማሳሰባቸው ተመልክተዋል።

ከክርስትያን ይሁዲ እና እስላም ሃይማኖት መሪዎች ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ግዜ ሁሉም በነዚህ አበይት ሃይማኖቶች መካከል ቀጣይ ውይይት እንዲካሄድ ሁሉም ዝግጁ መሆናቸው እንደገለጡላቸው አመልክተው፡ ዝግጅነቱ ለሰላም አቢይ ተራ እንደሚኖረው እምነታቸው መሆኑ ገልጠዋል።

ኢየሩሳሌም ውስጥ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንገሊካዊት እና ሉተራዊት አብያተክርስትያናት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይትም ለክርስትያን አንድነት የሚረዳ እና ተስፋ ሰጪ መኖሩ ጠቁመው፡ የሰው ልጅ ህልውና ወደ ብቸኛ እግዚአብሔር መጓዝ መሆኑ ጠቅሰው፡ መከባበር እና መቻቻል ለሰው ልጅ ሕብረት እንደሚረዳ መግለጣቸው ተነግረዋል።

አሉታውያን ነገሮች እና እንቅፋቶች ሁሉ ተወግደው አንድ ቀን በዚሁ አከባቢ ሰላም እንዲሰፍን እንደሚጸልዩ እና ለሰላም የሚረዳ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውም እንደገለጡ ተነግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፡ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ከቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ ጋር ወደ መሃከለኛው ምስራቅ መጓዛቸው የሚታወስ ሲሆን፡ ስለ ሐወርያዊ ጉብኝቱ መግለጫ መስጠታቸው ተመልክተዋል።

እሳቸው እንዳሉት ፡ ሐወርያዊ ጉብኝቱ የተስፋ የሰላም እና የማበረታቻ ዑደት መኖሩ እዚያው ያሉ ክርስትያን ማሕበረ ሰቦች መጐብኘት መሆኑ ጠቅሰው የክልሉ አበይት ሃይማኖቶች ማለትም ክርስትና ይሁዳዊ እና እስላም የሰላም እና የዕርቅ መሳርያ እንዲሆኑ በዚሁ አኳያ በጋርዮሽ እንዲሰሩ የሚጠይቅ ሐወርያዊ የሰላም መልእክት አድራሲ ነበር።

የቫርቲካን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ አያይዘው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከየእስራኤል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ነተንያሁ እና ከየፍሊስጢኤም ራስ ገዝ መሪ ማሕሙድ ዓባስ ጋር ሰላም ትኩረት የሰጠ ያደረጉት ውይይትም ስኬታማ መኖሩ ዋና ጸሐፊው ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።

በሊባኖስ የቅዱስ ዮሴፍ ዩኒቨርሲቲ የኢስላም ጉዳይ ፕሮፈሶር ኢየሱሳዊ አባ ሳሚር ቃሊል ሳሚር በበኩላቸው በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ፡ በክልሉ የፍትህ መጓደል እስራኤል እና ፓለስጢና የሚለይ ግድግዳ መሰራት አስከፊነት በተመለከተ ያደረጉት ንግግር ሐቅ የሚያንጸባርቅ እና ህሊና የሚነካ መኖሩ በበኩላቸው እንደገለጡ ተነግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.