2009-05-15 13:31:31

የበርማ የተቃዋሚው የፖለቲካ ሰልፍ መሪ ዳግም በወህኒ ቤት መታጐር


በበርማ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሰልፍ መሪና የሰላም ኖቨል ተሸላሚ አንግ ሳን ሱ ክዪ ባለፈው ሳምንት ካለ ፍቃድ ባንድ የአሜሪካ ዜጋ ተጎብኝተዋል በሚል ክስ ነው። RealAudioMP3 ይህ ደግሞ የቁምስ እሥር ውሳኔ የሚጥስ ድርጊት ነው በማለት ያገሪቱ ወታደራዊው መንግሥት ከነበሩበት የቁም እስረኛነት ወደ ወህኒ ቤት እንዲታጎሩ ማድረጉ ተገለጠዋል። RealAudioMP3

የእሳቸው መታሠር በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ አቢይ ቅሬታ ማሳደሩና ከተለያዩ መንግሥታትና የግበረ ሰናይ ማኅበራት ጭምር ወታደራዊው መንግሥት የወሰደው ውሳኔ የሚቃወምና የሰላም ኖቤትል ተሸላሚ አንግ ሳን ሲ ክዪ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነጻ ይለቀቁ ዘንድ ጥሪ እየተላለፈ ነው።

ስለ ጉዳይ በማስመልከት በኢጣሊያ ላምነስት ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማህበር ቃል አቀባይ ሪካርዶ ኑሪ፣ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ ሁሌ በያመቱ በሳቸው ላይ የተበየነው የቁም እስረኝነት ውሳኔ የሚያበቃለት ዕለት በተቃረበበት ወቅት የአገሪቱ ወታደራዊ መንግሥት የዚህ ዓይነት አሰናካይ ችግር መፍጠር ተለምዶው ነው፣ ስለዚህ የሚያስገርም አይደለም፣ የሚያሳዝነው የእስያ አገሮች ማኅበር የበርማው ወታደራዊ መንግሥት እየፈጸመው ያለው የሰብአዊ መብት መጣስ ተግባሩ በግድ የለሽነት ማየቱ ነው። ይህ ደግሞ ለበርማው መንግሥት ከለላ ስለ ሆነለት ጉዳዩ አለ መፍትሔ ቀርተዋል።

ከ 20 ዓመት በፊት ተካሂዶ በነበረው ሕዝባዊ ምርጫ አሸናፊ የሆነው በአውንግ ሳን ሱ ክዪ የሚመራው ብሔራዊ ለዲሞክራሲ ኅብረት በወታደራዊ ኃይሎች ሴራ ሳቢያ የፖለቲካው ሰልፍ የበላይ አካላት ሁሉም በወህኒ ቤት እንደታጎሩና አውንግ ሳን ሱ ክዪ 13 ዓመት በወህኒ ቤት ካሳለፉ በኋላ ስድስት ዓመት በቁም ታሳሪነት ቆይተው ይኸው ወደ ወህኒ ቤት እንዲመለሱ ተደርገዋል፣ ብዙ የዚህ የፖለቲካ ሰልፍ የአመራር አባላት ተሰደዋል በወህኒ ቤትም ታጉረዋል፣ የራስ ሰብኣዊ መብትና ፈቃድ እየተጣሰ ለሌሎች ሰብአዊ መብትና ፈቃድ መከበር መታገል ቀላል አይደለም፣ ስለዚህ ከመሰደድ ባገራቸው ሆነው ለራሳቸው ሳይሳሱ ለዚህ ለላቀው ዓላማ የሚታገሉ ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.