2009-05-15 12:15:04

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አሥራ ሁለተኛው አገራት አቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞ ዛሬ ይፈጸማል። 15.05.09


ቅዱስነታቸው ባለፈው ዓርብ እ.አ.አ. ግንቦት 8 ቀን 2009 ዓ.ም. የጀመሩት መንፈሳዊ ሓዋርያዊ ንግደት ዛሬ ዓርብ ግንቦት 15 ቀን ሊፈጸም ነው።

በዛሬው ውሎአቸው ብዙ ሓዋርያውያን ጉብኝቶች ፈጽመዋል። የተለያዩ ጥልቅና ትምህርት ሰጪ ንግግሮችም አሰምተዋል።

ዛሬ የክርስትያን አንድነት የሚያጐላ ግኑኝነት ለማካሄድ ወደ ግሪክ ኦርቶዶክስ ሓዋርያዊ መንበረ ፓርትያርክ ሄደዋል። እዛ በደረሱበት ጊዜ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሦስተኛ በክብር ተቀብለው የክርስትያን ማኅበር ወካዮች ወደሚሰበሰቡበት ‘‘ዙፋን’’ በሚል ስያሜ ወደሚጠራው አደራሽ ሸኝተዋቸዋል። RealAudioMP3








All the contents on this site are copyrighted ©.