2009-05-15 13:28:07

የር.ሊ.ጳ. የፍልስጥኤማውን መጠለያ ሰፈር ጉብኝት


ከትላትና በስትያ ግንቦት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቤተልሔም የሚገኘውን አይዳ በመባል የሚጠራው የፍልስጥኤም ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር በመጎብኘት ባሰሙት ንግግር፣ የእስራኤላውያንና የፍልስጥኤማውያን ክልል ይኸው ለሥልሳ ዓመት በግጭት እንዲታመስ ያደረገው፣ በመካከላቸው ያለው የጥላቻ መንፈስ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድጋፍ እና ትብብር እንዲወገድ ጥሪ አቅርበዋል። “ቅንና ዘላቂ ሰላም በሁለቱ ሕዝብ መካከል እውን እንዲሆን በመካከላቸው ያለው ማለቂያ ያጣው ጠበኛነት ማስወገድ እጅግ ወሳኝ ነው” እንዳሉም ተነግረዋል። RealAudioMP3

ቅዱስነታቸው በዚህ ከቤተልሔም 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የፍልስጥኤም ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት በተለያዩ RealAudioMP3 የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ዐቢይ ትኩረት እንደተሰጠው ተመልክተዋል። በመጠለያው ሠፈር ሙስሊሞችና ክርስትያን የሚገኙ ሲሆን በመጠለያው ሠፈር መኖር መፍትሔ የሚያሻው ሆኖ እያለ መቋጫ የሌለው ቀጣይ ሆኖ የተለመደ እየሆነ መምጣቱ ቅዱስነታቸው ቀርበው ለማረጋገጥ ችለዋል።

ለተፈናቃዮቹ ባሰሙት ንግግር “አንዳንዱ በወህኒ ቤት በመታጐሩ ወይንም ነጻነት በመጣሱ ምክንያት ብዙ ቤተሰብ ተለያተዋል፣ በተለያዩ የጥላቻ መንፈስ ምክንያት ብዙ ሕይወት አልቀዋል። እናንተ አንዲት ነጻና ልዑላዊት አገር ይኖራችሁ ዘንድ አቤት የሚለው ሕጋዊው ጥያቄአችሁ ገና አጥጋቢ ምልሻ አላገኘም፣ በዚህ ምክንያትም ደግሞ እናንተ የዚህ መጠለያ ሠፈር ነዋሪዎች በክልሉ በሚካሄዱት ግጭቶች አመጽ ዋና ተጠቂ የማኅበረሰብ ክፍል እንድትሆኑ አድርጎአችዋል” ካሉ በኋላ “ለዚህ ክልል ነዋሪው ሕዝብ ድጋፍና ትብብር ካለ ማቋረጥ በማቅረብ ላይ የሚገኘው ጳጳሳዊ የፍልስጥኤም ጉዳይ የሚከታተለው የተልእኮ ጽ/ቤትና በቅድስት መሬት ያለው ውጥረትና የሰላም እጦት እንዲቀረፍ የፍራንቸስኮስን መንፈሳዊነት በመኖር የሰላም መሣሪያ የሆኑት ሁሉ እየሰጡት ያለው የሰላም አስተዋጽዖ ከልብ አመስግነዋል።

“የዓለማችን አለማዊነት ትሥሥር ለምጣኔ ሃብቱና ለንግድ ልውውጥ እንጂ የሰው ልጅ ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስና የባህል ልውውጥ ክንዋኔ፣ የሕዝብ መገናኘት የማያነቃቃ እና ይኸንን የመሳሰሉ ለያይ አጥሮች ገና ሲገነቡ ማየቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው፣ ስንቱ ለያይ ግንቦች ተወግደው ሰላም እውን እንዲሆን የሚንቀሳቀሱት ሁሉ አስታውሰው፣ ሰላም እንዲረጋገጥ ካለ ማቋረጥ እንጸልይ” እንዳሉም ይታወሳል።

ለያይ አጥር በቀላሉ የሚገነባ ቢሆንም ቅሉ፣ ለዘላለም እንደማይኖር ሁላችን እናውቀዋለን። የሚፈርስበት ቀን ይመጣል፣ በቅድሚያ ጐረቤታችን የሚያገል በልባችን ውስጥ የምንገነባው አጥር ማስወገድ ይኖርብናል” እንዳሉም ተዘክረዋል።

“ሌላውን የማግለልና የማራቁ ቸል የማለቱ ምርጫ በቸርነት ሌላውን በመቀበል መንፈስ እንዲተካ ደግሜ ጥሪ አቅርባለሁኝ። ለብዙ ዓመታት እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ትግል አክትሞለት ለማየት ምኞቴ ነው” ካሉ በኋላ “ከታሪክ እንደምንማረው፣ ተቀናቃኝ ኃይሎች የጦር መሣሪያ ጋጋታቸውን አስወግደው ለጋራ ጥቅም መረጋገጥ አብረው ባንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ለመግባባት ዕንቅፋት የሚሆነውን ወደ ሰላም የማያደርሰው ግትርነት ወደ ጎን በማድረግ ብቻ ነው ሰላም ለማረጋግጥ የሚቻለው” እንዳሉም ተዘክረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም እ.ኤ.አ. የካቲት 15 ቀን 2000 ዓ.ም. የቅድስት መንበርና የፍልስጥኤም የራስ ገዝ መንግሥት የጋራው ድርገት የፈረመው ውል መሠረት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እውን እንዲሆን የሚደረገው ጥረት የጠቀሰ የቅድስት መንበር መገልጫ ለዚህ ክልል ሰላም መረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ሁሉ የሚደግፍ መሆኑ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.