2009-05-15 18:48:55

ቅዱስ አባታችን በናዝሬት ከተማ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና በናዝሬት ባሕር ኣጠገብ በሚገኘው ኮረብታ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋገቸው ተገለጠ። RealAudioMP3

ገሊላ የሚገኘው የእንግዶች መቀበያ ማእከል አስተዳዳሪ ኣባ ሪኖ ሮሲ አስተያየት ሲሰጡ “በዚሁ ቅዳሴ የተለያዩ ሥርዓት የሚከተሉት የካቶሊክ አብያተ ክርስትያን ምእመናን እንዲሁም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያን እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ምእመናን ጭምር ተሳትፈዋል። አጋጣሚው ለክልሉ ቤተ ክርስትያን በተለይ በገሊላ ለሚገኙት ክርስትያን እጅግ አስፈላጊና በቤተ ክርስትያን ደረጃ አቢይ ትርጉም ያለው ነው” ብለዋል።

“እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮውሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዚሁ ክልል ሓዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት በብዙ ሺሕ በሚገመቱ ወጣቶች የተሸኘ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ሁሉ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የነበረው ህዝብ በተለይ ደግሞ ወጣቱ የማኅበረ ሰቡ ክፍል ያሳየው የላቀ ተሳታፊነት የሚደንቅ ነው። ይህ እንዲሆንም የተደረገው ቅድመ ዝግጅቱም የሚያረካና በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የታየው መንፈሳዊነት ማራኪና እምነት የመሰከረ ነው” ብለዋል።

በመጨረሻም በገሊላ ያለው የኅብረ ሃይማኖት ማኅበራዊ ኑሮ የሚመስገን ነው። የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በክልሉ መገኘትና የሰጡት አስተምህሮ ስብከት ያሰሙት ንግግር ሁሉ ያለው የተረጋጋ ማኅበራዊ ኑሮ በሰላም በዕርቅ ይቅር በመባባል የተሳካ ይሆን ዘንድ የሚያነቃቃ ነበር። ከተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት የተዋጣለት እንደነበርና ውጤቱ ወዲያውኑ ባይሆንም በዝግታ እንደሚታይ አያጠራጥርም” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.