2009-05-13 14:03:38

ጳጳሳዊ የግብረ ተልእኮ ማሕበር


ጳጳሳዊ የተልእኮ ተግባር የበላይ መማክርት ጉባኤ ከትላትና በስትያ እ.ኤ.አ. ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. መጀመሩ ተገልጠ። ይህ ሮማ በሚገኘው በሳሊሲያን የጉባኤ ማእክል የተከፈተው ስብሰባ በንግግር የከፈቱት ስብከተ ወንጌል የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ መሆናቸው ተመለከተ። RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ዲያስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለተጋባእያኑ ያስተላለፉትን መልእክት አንብበዋል። መጽሓፍ ቅዱስ የቅድስና ሚሥጢርና የክርስቶስን መምሰል የሚስተነተንበት፤ ለሌሎች እርሱን ማስተዋወቅና ማቅረብ መሆኑ አብራርተዋል። የክርስቶስ ምስል በተናቁት በትናንሽ በድኾች ከማሕበረሰብ በተገለሉት ፊት የሚንጸባረቅ መሆኑ፣ ቅዱስ አባታችን ያሰመሩበትን አሳብ ገልጠዋል። የካህናት የገዳማውያን ሕንፀት በጣም አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ስለ ሕንፀት ጉዳይ አደራ ያሉትን ዳግም በማጉላት፣ ካህናት በመንፈሳዊነትና በባህል የጠለቀ ሕንፀት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል። የዚሁ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብጹዕ ኣቡነ ፒየርርጁዜፐ ቫኬሊ ይህ ጳጳሳዊ የግብረ ተልእኮ ማሕበር በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች እያከናወነው ያለውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አመስግነዋል። ማሕበሩ የአህዛብ ልብ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይከፍት ዘንድ የሚያነቃቃ ነው እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.