2009-05-13 14:00:31

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በጽርሐ ጽዮን


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የእስራኤል ሓዋርያዊ ጉብኝታቸውን በመቀጠል ትላትና በጽርሓ ጽዮን ተገኝተው ማርያማዊ ጸሎት ደግመዋል። እንዲሁም በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ካቴድራል ተገኝተው መካከለኛውን ምሥራቅ እያደማ ያለው ማለቂያ የሌለው ግጭት ተወግዶ ሰላም እውን ይሆን ዘንድ ጸልየዋል። RealAudioMP3

ቅዱስነታቸው በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውም በቅድስት መሬት ስላሉት ካቶሊክ ምእመናን ጉዳይ በሚመለከት “በዚሁ ክልል በህላዌአቸው በእምነታቸውና በአምልኮአቸው ልክ እንደ የሻማ ብርሃን ሆነው የክልሉን ቅድሳት ስፍራ የሚያበሩ ናቸው” ብለዋል። ለብፁዓን ጳጳሳትም “በእሳቸው ቅርበትና ድጋፍ ላይ እንዲታመኑና የሳቸውም ድጋፍ እንደማይለያቸው በማሳሰብ፣ የዚህ ክልል ማኅበረ-ክርስትያን ማሕበረሰብ የቅድመ አያቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የሰላም አንቀሳቃሽና ልኡካን ይሆኑ ዘንድ አደራ ብለዋል። ክርስትያኖች ሁሉ ለዚህ ክልል ማኅበረ-ክርስትያን ማሕበረሰብ ይጸልዩም ዘንድ ለመላው ዓለም ማኅበረ-ክርስትያን ደግመው ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም በዚሁ ክልል የሚገኙት የተለያዩ አብያተ ክርስትያናት የክልሉ መንፈሳዊ ቅርስ የሚወክሉ “በወንጌልና በተለያዩ ባህሎች መካከል ያለውን ውስጣዊ የመደጋገፍ ግንኙነት የሚያንጸባርቁ ስለሆኑ የቤተክርስትያን ተልእኮ በእግዚአብሔር የተጠሩትን ሁሉ ቅርብና ሩቅ ያሉትን ባንድ ጥላ ሥር እንዲሰባሰቡ በማድረግ ልዩና ብቸኛው የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንዲጸና የእግዚአብሔር ኩላዊው ፍቅር የሚያበሥሩ ናቸው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አያይዘውም “በግልም ሆኖ እንደ ማኅበረሰብ የዚሁ ክልል ሕዝብ ከእኔነትና ራስ ወዳድነት ተነጥሎ ቅድመ ፍርድና መፈራራትን የመሳሰሉትን መሰናክሎችን በመሻገር እራሳችንን ለሌሎች ለመስጠት ባለ መልካም ፈቃድና ቸር በመሆን ለመወጣት እንደሚቻል አብራርተዋል። ይህ ደግሞ በግልጽና በጽናት ክርስትያኖች ለተሰጣቸው ተልእኮ ታማኞች እንዲሆኑ ያደርጋል” ብለዋል።

ካህናትና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ገዳማውያንና ዓለማውያን ምእመናን በዚህ ቅዱሳት ሥፍራዎች የሚኖሩት ሁሉ የክርስትያኖች ሕይወት በተቀደሰው ሥፍራ ምን እንደሚመስል መስካሪዎች ናቸው። ለዚህም ዓቢይ ኃላፊነት እንዳላቸውም ገልዋል። በመጨረሻም “እንደ ዘማሪው ዳዊት ለኢስየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ” በማለት “ማለቂያ የሌለው የዚሁ ክልል ግጭት ጨርሶ ይነቀል ዘንድ ካለ ማቋረጥ እንጸልይ” በማለት ቡራኬ መስጠታቸው ተገልጠዋል። RealAudioMP3 RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.