2009-05-13 14:02:20

ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ የተደረገላቸው አቀባበል


ዘላቂው ደህንነት ከመተማመን የሚመነጭ በፍትሕ የሚገነባ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ከእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ ጋር በመገናኘት ባሰሙት ንግግር ጠቅሰዋል። በዚህ 300 እንግዶች በተገኙበት በርእሰ ብሔሩ ሕንጻ በሚገኘው የእንግዳ መቀበያ አዳራሽ በተደረገላቸው አቀባበል ባሰሙት ንግግር “ፍትሕ የሰላም ዋስ ነው” ብለዋል። RealAudioMP3

በየቀኑ ከፍትሕ የሚመነጭ ሰላም በዚሁ ክልል ይሰፍን ዘንድ ጸሎት እንደሚያደርጉና መከባበር መቀባበል ፍትሕና ሰላም የሚጠሙና አቤት የሚሉት ለዚሁ ክልል ሕዝብ ከውጭም ሆነ ከውስጥ ከሚነዙት የማስፈራሪያ ዛቻና ዓመጽ ነጻ ሆነው ዘላቂው መረጋጋት እውን ይሆንለትም ዘንድ ድምጼን ከፍ በማድረግ የሰላም ጥሪ አቀርባለሁኝ ብለዋል። “ሰላም በቅድሚያ የእግዚአብሔር ስጦታ በመሆኑ ስለዚሁ ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላምን ካለ መታከት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲፈልጉዋት አሳስበዋል። በምእመናን ማኅበረሰብ መካከል ያለውን የውሉድነት ኅብረት የሚያደፈርሰው፤ የእግዚአብሔር አቻ የሌለው አንድነቱን እንዳይታይ የሚያደርገው፤ መጠራጠር ውጥረት እና ጥላቻ ይወገድ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢየሩሳሌም የተለያዩ ዘር ያላቸው ማለትም አይሁድ ክርስትያን ሙስሊም ወደር የማይገኝለት ሰላማዊው ያብሮ መኖር ምስክርነት እንዲሰጡ ኃላፊነት እንዳላቸው ጐልቶ ይታያል። ይኽንን ዕድል ይጠቀሙ ዘንድ የተሰበሰቡባት አንድ እግዚአብሔርን በሚያመልኩ አህዛብ የሚመኙዋታ አገር ነች ብለዋል።

ደህንነት፤ አንድነት፤ ፍትሕ እና ሰላም በእግዚአብሔር ዕቅድ ዓቢይ ሥፍራ ያላቸው እሰይታዎች ናቸው። እነዚህ እሰይታዎችን ለማነቃቃት ለመኖርና በየዕለቱ ለመመስከር እንዲቻል፣ በፍትሕ አገልግሎት የሚሰጥባት አገር ወሳኝ ነች። ስለዚህ የአንዲት አገር ፍላጎት በፍትሕ ማገልግል መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ በበኵላቸው ባሰሙት ንግግር፣ ዓቢይ የሃይማኖት መሪና የሰላም አንቀሳቃሽ በማለት ር.ሊ.ጳጳሳትን አመጒሶዋቸዋል። በእስራኤልና በቅድስት መንበር መካከል ከጋራ መግባባትና ከዕርቅ መንፈስ የመነጨ ግኑኝነት እውን መሆኑም አስረዱ። ከእስላም ዓለምም የዚህ ዓይነት ግኑኝነት ይኖር ዘንድ በሩ ክፍት ነው ብለዋል።

አክለውም ሁላቸን አይሁዳውያን ክርስትያኖችና ሙስሊሞች በጠቅላላ አማኖች አሕዛብ የወቅቱ አንግብጋቢ ጥያቄ ሆኖ ያለው መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት የሚለው ጉዳይ ሳይሆን፣ ሃይማኖትና አመጽን መለያየት የሚለው ነው ብለዋል። በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት የእስራኤል ርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ፣ ቤተሰቦቻቸውንና እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. በእፍልስጥኤም ታጣቂ ሃይሎች እጅ የተጠለፈው የእስራኤል ወታደር አያት ቀርበው ለር.ሊ.ጳጳሳት በማስተዋወቅ ቅዱስ አባታችን በግጭት ሳቢያ በሚፈጠረው ችግር ለሚደርሰው ስቃይ ተካፋይ መሆናቸው እንደገለጡ ለማወቅ ተችለዋል።

በመጨረሻም በር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና በርእሰ ብሔር ሺሞን ፐረስ መካከል የገጸ በረከት ልውውጥ ማከናወኑ ተገልጠዋል።

RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.