2009-05-12 10:55:30

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በዮርዳኖስ የአማን መስጊድ ጐበኙ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ16ኛ ባለፈው ዓርብ በመካከለኛው ምስራቅ የጀመሩት የአንድ ሳምንት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደቀጠለ ነው።

የቅዱስነታቸው በዮርዳኖስ ቆይታ ሁለተኛ ቀን የአማን አል ሑሴን ቢን ጣላል ታሪካዊ መስጊድ መጐብኘታቸው፡ ከቅዱሰነታቸው ጋር የተጓዙ የቫቲካን መንግሮች ወኪሎች አስታወቁ።

መስጊዱ ውስጥም ከሀገሪቱ የኢስላም ሃይማኖት መሪዎች ጋር መገናኘታቸው እና መስጊዱ ውስጥ ባደረጉት ንግግር፦ “ሃይማኖቶች በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመረኮሱ እና የሰው ሰብአዊ ክብር ጠባቂ ከሆኑ፡ ከየፖሊቲካ ርዕዮተ ዓለም ተጽዕኖ ነጻ ከሆኑ፡ ለኅብረተሰብ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ” እንዳሉ ወኪሎቹ አስገንዝበዋል።

የዮርዳኖስ ልዑል ጋዚ ቢን መሐመድ ቢን ጣላል በዚሁ ግንኙነት ተገኝተው መኖራቸውም ተመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ፡ የሃይማኖት ነጻነት መብት ከየአምልኮ ነጻነት እንደሚልቅም ለየኢስላም ሃይማኖት መሪዎቹ መግለጣቸው ወኪሎቹ አስገንዝበዋል።

በዚሁ በየአማን መስጊድ፣ የእንተ ላዕለ ኵሉ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ እና በሀገሪቱ የኢስላም ሃይማኖት መሪዎች መካከል የተካሄደ ግንኙነት፡ የውስጠ ሃይማኖት ውይይቱ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በዓለም ላይ ሰላም ለማስፈን የቀሰቀሰ አዎንታዊ ግንኙነት መኖሩ የቫቲካን እና የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን አመልክተዋል።

በነዚህ መገናኛ ብዙኀን መሠረት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የዮርዳኖስ ልዑል ጋዚ ቢን ሙሐመድ ቢን ጣላል፡ የክርስትያን እና የኢስላም ሃይማኖት ውይይት በሁለቱ ሃይማኖቶች መሀከል መረዳዳት መተባበር እና መከባበርን እውን እንዲሆን፡ መወሰድ ያላቸውን እርምጃዎች እንደሚያመላክትም ተገልጠዋል።

በፖሊቲካዊ ጥቅም ያልተነካ ንጹህ የኢስላም ሃይማኖት ትምህርት፡ ለእድገት እና ለሰላም እንደሚያግዝ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መግለጣቸው እና፡ አማን ውስጥ ያለው ክርስትያን እና የኢስላም ተከታዮች ተማሪዎች አቀፍ ዩኒቨርሲቲ የሁለቱ ሃይማኖቶች ባህሎች፡ አገናኝ መሆኑ እና፡ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች የመቻቻል የሰላም እና የአብሮ መኖር ዕድል እንዲሰጥ ያላቸውን ተስፋ መግለጣቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

ሃይማኖት፡ ድንቁርና እና አመጽ ማገለገል ከተገደደች፡ ባህልዋ እና እውነተኛ ዓላማዋ እንደሚበላሽ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጠቅሰው፣ እዚህ የሰው አእምሮ መሰረቁ እና የሃይምኖት ዋነኛ ዓላማ ተቀልብሶ እንደሚታይ ማስገንዘባቸው ተነግረዋል።

በተጨማሪ ክርስትና እና ኢስላም ግብረ ገብነት ላይ የተመረኮሰ ሳይንሳዊ ጥናት በጋራ ካካሄዱ፡ ለተሻለ ትውውቅ እንደሚረዳቸው አውስተው፡ ሁለቱ ወገኖች አድማሳዊ የሰው መብት ስምምነት በጋራ ለማስከበር ጥረት ለማካሄድም ዕድሉ እንደሚገጥማቸው ማውሳታቸው መገናኛ ብዙኀኑ አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዮርዳኖስ ከክርስትያን ተማሪዎች ጋር ማዳባ ላይ መገናኘታቸው እና ለተማሪዎቹ ባሰሙት ንግግር፡ ፍትሕ የነገሠበትና ሰላማዊ ኅብረተሰብ ለመገንባት ተጠርታችሁዋል እና ግፉበት ማለታቸው ተመልክተዋል።

ሃይማኖት የመከፋፈል መንሥኤ ነው የሚል አቋም የተላበሱ ግለ ሰዎች እንዳሉ የጠቆሙት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሃይምኖት የመለያየት ምክንያት እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ያላቸው የተሳሳተ አቋም ያላቸው መሆናቸው በመግለጽ፡ ሃይማኖት የሰላም የአንድነት እና የዕርቅ መሣርያ መሆኑ ማስገንዘባቸው ከቦታው ተመለክተዋል።

የተለያዩ የሃይማኖት ባህሎች በሚከተሉ ሰዎች መካከል አለመቻቻል እና ህውከት እንደሚታይ ቅዱስነታቸው ጠቅሰው፡ መንስኤው፡ ሃይማኖት የፖሊቲካ መሳርያ እና የስልጣን መወጣጫ ስለሚጠቀሙት መሆኑን ለተማሪዎቹ ካደረጉት ንግግር ለመረዳት ተችለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ንግግራቸው በማያያዝ በቅድስት መንበር፡ በተለያዩ ሃይማኖቶች ውይይት የሚያካሄድ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እና ተቀማጭነቱ ዮርዳኖስ ባደረገ የኢስላም ምሁራን ቡድን መካከል ቀደም ሲል የተጀመረው ውይይት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑ ማመልከታቸውም ተነግረዋል።

138 የኢስላም ሃይማኖት ምሁራን ያቀፈ ቡድን ኮመን ዎርልድ የጋራ አለም ሰይሞ ቀደም ሲል የጻፈው መልእኽት እና የራስቸው ‘ደዩስ ካሪታስ ኤስት’ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚለውን የመጀመርያ ሐዋርያዊ መልእክታቸው ጋር የመጣጣም አዝማምያ እንዳለው ቅዱስነታቸው እንዳብራሩም ከአማን ዮርዳኖስ የመጡ ዜናዎች አስታውቀዋል።

ሰብአዊ ክብሮች የሰብአዊ መብቶች ምንጮች መሆናቸውንም ገልጠዋል። ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ ረፋድ ላይ የዮርዳኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው አጠቃልለው እስራኤል በተመሳሳይ ለመጐብኘት ከዮርዳኖስ ወደ ተልአቪቭ ተሻግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.