2009-05-11 13:40:45

የእናቶች ቀን ትላትና ታስቦ ዋለ


እ.ኤ.አ. ትላትና እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ.ም. የእናቶች ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ተረሰ ደ ሆመስ እና ማመ ኔላ ረተ የተሰኙት ሴቶችን የሚንከባከቡት የግብረ ሠናይ ማህበራት 4 ሺሕ የአይቨርይ ኮስት ሴቶችን ለመርዳት በማቀድ ለዚህ ዓላማ የተለያዩ የማነቃቂያ መርሃ ግብሮች መወጠናቸው ለማወቅ ተችለዋል።

የተረሰ ደ ሆመስ የግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ በነዴታ ካፐሊ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ ለነዚህ 4 ሺሕ ሴቶች መርጃ የሚውል እቅድ በመቀጠል 20 ሺሕ ሴቶችን የሚያጠቃልል እንደሚሆን ያለመና እነዚህ ሴቶች በስተ እርግዝናቸው ወቅት ሕክምና እንዲያገኙና ተገቢ ሕክምና በማግኘትም የራሳቸውንና የሚወለደውን ሕጻን ጤና ዋስትና ለመስጠት እንዲታገዙ የሚያደርግ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ በዚህች አገር ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የጤና መታወክ ሳቢያ ብዙ እናቶችና የሚወለደውም ሕጻን ላደጋ እንደሚጋለጥ በመጥቀስ እቅዱ ይኽንን ለሴቶችና ለሚወለደው ሕጻን የሚደግፍ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.