2009-05-11 13:39:27

የቫቲካን ቤተ መዘክሮች አስተዋጽዖ


ትላትና እሁድ የቫቲካን ቤተ መዘክሮች ለመጎብኝተት የተከፈለው የመግቢያ ቲኬት በኢጣሊያ አብሩዞ ክፍለ ሃገር ተከስቶ በነበረው የመሬት መናወጥ አደጋ ለተጎዳው ሕዝብ መርጃ እንደሚውል ተገለጠ።

የቫቲካን ቤተ መዘክሮች አስተዳዳሪ ፕሮፈሶር አንቶኒዮ ፓውሉቺ ስለዚሁ የግብረ ሰናይ እቅድ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ እቅዱ ያነሳሱት የቫቲካን ቤተ መዘክሮች ሠራተኞች ሲሆን፣ የቫቲካን ቤተ መዘክሮች እሁድ አገልግሎት የማይሰጡ ሆነው እያሉ፣ ሠራተኞቹ የእረፍት ጊዜአቸውን ለዚህ ለተቀደሰው አላማ ለማዋል በማቀድ፣ እሁድ ክፍት እንዲሆንና ገቢውም በርእደ መሬት ለተጠቃው ለአብሩዞ ክልል ነዋሪ ህዝብ መርጃ እንዲውል በራስ አነሳሽነት ያከናወኑት መሆኑ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.