2009-05-11 13:37:52

ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል


ቅዱሱ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በዮርዳኖስ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት ትላትና አማን በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በሚጠራው የግሪክ መልካዊት ካቴድራል የሰርክ ጸሎት በመምራት ማጠናቀቃቸው ተገለጠ።

ቅዱስነታቸው በካቴድራሉ እንደደረሱም በግሪክ መልካዊት ቤተ ክርትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ጎርጎሪዮስ ሶስተኛ ሌሀምና በምክትላቸው ብፁዕ አቡነ ያሰር አያች አቀባበል እንደተደረገላቸውም ሲነገር፣ በዚህ በመሩት ጸሎተ ሰርክ ባሰሙት ስብከት፣ እውነተኛው የእምነት ቃል ወደ ውህንደትና ፍትሕ ፍቅርና ሰላም ይመራናል በማለት፣ ሞትን አሸንፎ በተነሣው የጌታ ብርሃን ተመርተን በእርሱ ተስፋ አሸብርቀን በእርሱ እውነትና ፍቅር ተሞልተን የምንሰጠው ምስክርነት በጉዟችን ለምንገናኛቸው ሁሉ በረከትን ያሰጣል ካሉ በኋላ፣ የዚህች አገር ሙስሊሞችና ክርስትያኖች በጠቅላላ በዚህች አገር ንጉሥ መልካም ፈቃድ መሠረት የሌሎች አገሮችን ተፈናቃዮችን በማስተናገድ የሚሰጡት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚደነቅ ነው ብለዋል፣ የዚህች አገር ክርስትያን ማኅበረሰብ ህላዌ፣ የተስፋ ምልክት መሆኑና ይህ ደግሞ ክርስትያን ማሕበረሰብ በራሱ ብቻ ሳይታጠር የሌሎችን ችግርና ስቃይ የራሱ በማድረግ የፍቅር አገልግሎት እንዲሰጥ እያደረገውም ነው ብለው፣ በመጨረሻም ዘመኑ በጣም የተወሳሰበ በመሆኑም ወጣቱን ትውልድ መንገዱን እንዲስት የሚያደርግና የዋሁን እድሜውን ተገን በማድረግ የሚሰጠው የተዛባ አደናጋሪ መርህ ለወላጆች ምንኛ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ ጠቅሰው፣ ክርስትያኖች እይታቸውን ወደ ክርስቶስ በማቅናት፣ በእርሱ ብርሃን ክፋትንና የተነጠቀውን ገሩ የወጣቱ እድሜ ከአሳሳቹ መንገድ እንዲድኑ በማድረጉ ያገልግሎት ሚና አቢይ ሃላፊነት እንደሚጠበቅባቸውና እያከናወኑት ያለውን አገልግሎት የሚመሰገን ነው ብለዋል።

የምሥራቅ ቤተ ክርስትያን ጥንታዊው ሕያው ቅርስ ኩላዊት ቤተ ክርስትያንን ባለ ጸጋ የሚያደርግ መሆኑና ይህ ቅርስ ታፍኖ ተካፋይነት የሌለው ሆኖ መታቀብ የለበትም ካሉ በኋላ፣ የዚህ ክልል ክርስትያን ማህበረሰብ ልክ ያዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በፊት በአንጽዮኪያ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትያን ተብለው ከተጠሩትና ትተዉት ከሄዱት የተቀደሰው ባህል ከሚያንጸባርቀው ከጥንታዊው ያንጽዮኪያ ፓትሪያርክ ጋር የጠበቀ ትሥሥር ያላቸው መሆናቸውንም አመልክተው ምንም’ኳ አናሳው የማህበረሰቡ ክፍል ብትሆኑም እውቅና ያላቸሁ የትንሳኤ ክርስቶስ ሕያው የሚደርገው ብርሃን ዳግም እንዲያበራ የምታደርጉ ናቸሁ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.