2009-05-11 13:36:06

ቅዱሱ አባታችን በነቦ ተራራ ለሙሴን የመታሰቢያ ባሲሊካ ጎበኙ


በቤተ ክርስትያንና በአይሁዳውያን መካከል ያለው አንድነት ከማይነጣጠለው ዝምድና የመነጨ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በኔቦ ተራራ ለሙሴ መታሰቢያ በተሠራው ባሲሊካ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር በማብራራት፣ የዚህ ክልል አቢያተ ክርስትያናት ከጥንት ጀምረው በሊጡርጊያቸው በብሉይ ኪዳን የሚገለጡትን አበይት አበው የሚዘክሩና ይህ ደግሞ በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል ያለውን ኅብረትና ቀጣይነት በጥልቀት የሚመሰክር ነው ብለዋል።

በአይሁድና በክርስትያን መካከል የእርስ በእርስ መከባበር ተረጋጋጦ የእግዚአብሔር ቃል የሰላም አገልጋዮች እንድንሆን ለሚጠራን አላማ በመተባበር ለመጽሐፍ ቅዱስ ባለን ፍቅር አማካኝነት እንቅፋት የሚሆነን ሁሉ ልንቀርፍ ተጠርተናል እንዳሉ ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው በባሲሊካው እንደደረሱም የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያሰሙት ኣባ ሮድርገዝ ካርባሎ ባንድ ወቅት የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን በመከተልና በርእሱ እንደተመሩ ሁሉ ዛሬ በበረሃ እንዳለን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚመራንን እንሻለን ማለታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ይኸንን ኖሎአዊ ቃል አቢይ ግምት በመስጠት ሙሴን ማስታወስ ማለት ዓይናችንን ወደ ላይ በማቅናት የጥንቱን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በማድነቅ በነጻነት ለማመስገን ብቻ ሳይሆን እርሱ ለኛና ለመላው ዓለም ያሰበውን በእምነትና በተስፋ መጠባበቅ ማለት ነው ብለዋል።

እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ከኃጢአትና ከባርነት ወደ ሕይወትና ነጻነት የሚወስደውን መንገድ እንድንከተል እንደ ሙሴ በየስማችን ጠርቶናል፣ የሙሴ አብነት እኛም የዚህ የማያቋርጥ የእግዚአብሄር ሕዝብ በታሪክ ያደረግገው ጎዞ ተካፋዮች ነን። በዚህች አጭር እድሜአችን እንደ ሙሴ የእግዚአብሔር እቅድ ፍጻሜውን ለማየት የማንችል ብንሆንም ቅሉ፣ በተጠራንበት መንገድ ታማኞች በመሆን በእምነትና በታማኝነት ልክ እግዚአብሔር ለሙሴ ስሙን በመግለጥ ከጎኑ ሆኖ እንደመራው ሁሉ እኛንም ይመራናል፣ በዚህ ጉዞ ጸንተን በተስፋና በደስታ እንድንጓዝም ዘንድ ኃይሉንም ይሰጠናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.