2009-05-08 13:37:25

ጳጳሳዊ የስነ መጽሓፍ ቅዱስ መንበረ ጥበብ


ጳጳሳዊ የስነ መጽሐፍ ቅዱስ መንበረ ጥበብ የተመሠረተበትን 100ኛውን ዓመት ትላትና ማክበሩ ሲገለጥ፣ ይህ እ.ኤ.አ. በ 1909 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 10ኛ መልካም ፈቃድና ውሳኔ መሠረት ተቋቁሞ ሃላፊነቱንም ለእየሱሳውያን ማኅበር ተሰጥቶ ሥራውን አንድ በማለት መጀመሩ ሲገለጥ፣ በሮማና ቀጥሎ በእየሩሳሌም ተቋቁሞ በስነ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ምርምር ወደር የማይገኝለት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

የዚሁ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ የተመሠረተበት 100ኛው ለማክበር እዚህ ሮማ በጳጳሳዊ ግሬጎሪያና መንበረ ጥበብ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ጳጳሳዊ የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዜኖን ግሮቾሎውስኪ የተገኙበት ጉባኤ መካሄዱ ተገልጠዋል። ጉባኤው ከመከፈቱ በፊት በቅዱስ ኢግናጽዮስ ቤተ ክርስትያን መስዋዕተ ቅዳሴ መቅረቡም ተገልጠዋል።

የዚህ ጳጳሳዊ የስነ መጽሐፍ ቅዱስ መንበረ ጥበብ ዓላማ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ብፁዕ ካርዲናል ዜኖኖ ግሮቾለውስኪ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያብራሩ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመጨረሻው ተካሄዶ በነበረው የካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ደይ ቨርቡም ቃለ እግዚአብሔር የተሰኘው ውሳኔ በመጥቀስ መጽሓፍ ቅዱስ ስነ ጽሑፋዊና ታሪካዊ ጥናት መሠረት ሊተነተን ተገቢ ነው፣ ሆኖም ግን ይህ ለብቻው በቂ እንዳልሆነ ባሰሙት ንግግር ጠቅሰው ቲዮልጎያዊ ማለትም በቤተክርስትያን አገባብ ቃለ - እግዚአብሔር ቅዱስ መጽሐፍ ለብቻው ሳይሆን በትውፊትና በቤተክርስትያን ሕይወት የእግዚአብሔር ህልውና እንደሚናገርም ማብራራታቸው አስታውሰው፣ ስለዚህ ቅዱስ መጽሓፍ የቤተክርስታያን ትውፊትና ሥልጣናዊ ትምህርት ካለ መነጣጠል አንዱ ብሌላው ላይ ተጽእኖ ሳያደርግ በጥምረት የቅዱስ መጽሐፍ ስነ ትንተና መሠረት ናቸው ብለዋል።

ቀጥለውም የስን ቅዱስ መጽሐፍ ሊቅ ፕሮፈሶር ማውሪሰ ጂልበርት የቅዱስ መጽሕፍ ስነ ትንተና ጠለቅ ባለ መልኩ እንዲከናወንና ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥራ አንደኛ በማበረታታት ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ 12ኛ ድቪኖ እፍላንተ ስፒሪቱ በመንፈስ ቅዱስ አስተንፍሶ ተነቃቅተው በተሰኘው እ.ኤ.አ. በ1943 ዓ.ም. በደረስዋት ዓዋዲት መልእክት አማካኝነት የስነ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተመራማሪዎችና ተንታኞችን አማኞችና የቅዱስ መጽሐፍ ቲዮሎጊያ ጥናት የሚያቀርቡ መሆናቸው ሳይዘነጉ ሳይንሳዊ ሥራቸው እንዲያጎለብቱ ማሳሰባቸው በማስረዳት የሰጡት መሪ ቃል የዚህ ተቋም የሳይንስ ምርምር ሂደቱ እንዳነቃቃው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.