2009-05-08 13:41:20

የኢራቅ ከለዳዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ተጠናቀቀ


በኢራቅ ሲካሄድ የሰነበተው የከለዳዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ የኢራቅ አንድነት እንዲበረታና ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ በማቅረብ መጠናቀቁ ተገልጠ። ይህ በአንካዋ ከተማ የተካሄደው ሲኖዶስ፣ በባገሪቱ ሰላምና አንድነት መረጋጋት ዳግም እውን እንዲሆን እና በክልሉ ባለው ችግር ሳቢያ ለስደት የተዳረጉት የኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች ወደ አገራቸው ለመለለስ የሚያግዝ ሁኔታ ይፈጠርላቸውም ዘንድ በማሳሰብ፣ በተጨማሪም የኢራቅ ተፈናቃይና ስደተኛው ዜጋ ችግሩ ተወግልዶለት እለታዊ ኑሮውን በሰላም እንዲመራ በማድረጉ እቅድ የሚተባበሩትን ሁሉ ሲኖዶሱ በይፋ ማመስገኑ ተገልጠዋል።

የባግዳድ ከለዳዊት ቤተ ክርስትያን ሰበካ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሽለሞን ዋርዱኒ የኢራቅ እያንዳንዱ ጎሳ የኢራቅ ህብረት መግለጫ መሆኑ ጠቅሰው፣ ቋዋሚው የፓትሪያርካዊ ምክር ቤት ባመት ሁለቴ ውይንም ሦስቴ በመሰብሰብ በተለያየ ወቅት ለሚካሄዱ ሲኖዶሶች ከወዲሁ የውይይት ነጥቦች እያሰባሰበ እንደሚሄድም ገልጠው፣ ሲኖዶሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ተሸኝቶ ለቤተክርስትያንና ለምእመናን ጥቅም መከናወኑና ልባዊ መቀራረብ የታየበትም ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.