2009-05-08 13:43:18

የሕገ ወጥ ስደተኞች ወደ ሊቢያ መመለስ


ከትላትና በስትያ 227 የሕገ ወጥ ስደተኞች ኢጣሊያ ለመግባት በላምፔዱሳ የባህር ክልል የነበሩት በጠቅላላ ወደ መጡበት መሸኘታቸው ሲገለጥ፣ የነዚህ 227 የሕገ ወጥ ስደተኞች ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ ውሳኔውና ሂደቱንም በተመለከተ የኢጣሊያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ሮበርቶ ማሮኒ ትላንትና ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ተገልጠዋል።

ማልታና ኢጣሊያ የሕገ ወጥ ደተኞች ወደ መጡበት መሸኘት በሚል ውሳኔ መስማማታቸውም ለማወቅ ሲቻል። ይህ ውሳኔና በተለይ ደግሞ ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ የተደረጉት የሕገ ወጥ ስደተኞች ዕጣ እድል አሳሳቢ መሆኑ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና የተፈናቃዮች የበላይ ድረገት ያለውን ስጋት ይፋ አድርገዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.