2009-05-08 13:39:34

ዛሬ ተስፋን ማስተማር


የሮማ ሰበካ ከላዚዮና የሮማ ጳጳሳዊ መናብረተ ጥበባት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያነቃቃው “ዛሬ ተስፋን ማስተማር” በተሰኘው ርዕሰ ጉዳይ የሚወያይ ዓውደ ጥናት ትላትና በቫቲካን የሮማ ኅይነተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ በተገኙበት መከፈቱ ተገለጠ።

የሰው ልጅ ለተሟላ እድገት ለማነጽ የሚያጋጥሙ እክሎችና የሚመረጠው የትምህርትና የህንጸት አሰጣጥ ሂደት ጠለቅ አድርጎ የሚወያይ ዓውደ ጥናት መሆኑ ታውቀዋል።

ስለዚሁ ዓወደ ጥናት በማስመልከት የሮማ ሰበካ የመናብረተ ጥበባት ሓዋርያዊ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት ተጠሪ ብጹዕ ኣቡነ ሎሬንዞ ሌውዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ አስተማሪዎች ለዘመኑ ወጣት ከተጨባጩ ሁኔታ ጋር የሚገኛና ከእለታዊ ኑሮ ገጠመኝ ጋር የሚዛመድ ህንጸት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ቤተሰቦችም በዚህ ዘርፍ አቢይ ሚና እንዳላቸውም አስታውሰው፣ ይህ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ የመጪው ሕይወቱን ከወዲሁ ዓልሞ ቅርጽ እያስያዘ እንዲሄድ ያግዘዋል። ይህ ደግሞ ዛሬ ተስፋን ማስተማር በተሰኘው ርእስ ሥር የሚወያይ ዓውደ ጥናት እንደሚያሰምርበት ነው ብለዋል።

በዚሁ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ዓውደ ጥናት የሮማ መንበረ ጥበብ መምህር ማሪና ዳማቶ አስተምህሮ ከሚያቀርቡት ውስጥ ሲሆኑ፣ ቤተሰብ አስተማሪና ተማሪ ተያዘው የሚሄዱ ተመሳሳይ ነገር ግን የተለያየ ሃላፊነት ያላቸው አብረው የሚኖሩ ናቸው ካሉ በኋላ፣ በማስተማር ዘርፍ ሃላፊነት ያለባቸው ሁሉ የዘመኑ ወጣት በዚህ የስነ ማነጻጻርና የዲጂታል ስልት አንድ ባለበትና እደ ጥበብ አይሎ በማደግ ላይ በሚገኝበት ዘመን የተወለዱ በመሆናቸው ስለዚህ የሚያጋጥሙት እከሎች ቀላል አይደለም፣ ስለዚህ ወጣቱን ተስፋን በማስተማር የሃላፊነት ባለ ቤት ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.