2009-05-08 13:35:30

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የኤል ሳልቫዶር ርእሰ ብሔር ትላትና ተቀብለው አነጋገሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ዮርዳንስንና ቅድት አገርን ለመጎበኘት ከመነሣታቸው በፊት፣ ትላትና የኤል ሳልቫዶር ርእሰ ብሔር ኤሊያስ አንቶኖዮ ሳካ ጎንዛለስን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ማህተም ክፍል አስታወቀ።

በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት ስለ ኤልሳልቫዶር የውስጥ ጉዳይና እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በተመለከቱ ርእሶች መወያየታቸው ለማወቅ ተችለዋል። የሬፑብሊካዊት ኤል ሳልቫዶር ርእሰ ብሔር በተካሄደው ግኑኝነት አገራቸው በዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ መድረክ እያካሄደችው ያለው ትብብር እንዲሁም የተደራጁትን የወንጀል ቡድኖችን ለማጥፋት የአገሪቱ መንግሥት እያከናወነው ያለው ትግል፣ የኤል ሳልቫዶር የትምህርት ጉዳይ ለማሻሻል ስለ ስደተኞችና ማሕበራዊ ጉዳዮች በማነቃቃት ረገድ እየፈጸመችው ያለው ሂደት ማብራራታቸው ተገለጠ።

በመጨረሻም የኤል ሳልቫዶርና የቅድስት መንበር ግኑኝነት አመርቂና የተዋጣለት መሆኑ ከግኑኝነት በኋላ የቅድስት መንበር የዜናና ማህተም ክፍል ያሰራጨው መግልጫ ሲያመለክት መንፈሳዊነት ለማበልጸግ ብሎም ሰላምንና ብሔራዊ እድገትን ለመጨበጥ ጥረት መደረግ እንዳለበት ቅዱስ አባታችንና የኤል ሳላቫዶር ርእሰ ብሔር አስፈላጊ መሆኑ በጋራ አስምረውበታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.