2009-05-06 14:39:20

የፐሩ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት፡


የፐሩ ጳጳሳት ቫቲካን ውስጥ ቪሲታ አድሊሚና ማለት ሐዋርያዊ ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸው ተመልክትዋል ። እንደሚታወሰው ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአምስት ዓመት አንድ ግዜ የቅዱሳን ጴጥሮሰ - ጳውሎስ መቃብሮች ለመሳለም እና አብያተ - ክርስትያኖቻቸው በተመለከተ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለመወያየት ቫቲካንን ይጐበኛሉ።

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ እስከ ግንቦት ወር 23 ቀን እንደሚዘልቅ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል። በላቲን አመሪካ ሄሚስፈር የምትገኘው ፐሩ 28 ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባት እና ከነዚህ በመቶ ሰማንያ ስምስት ካቶሊካዊ እምነት የሚከተል መሆኑ ይታወቃል።

በፐሩ የትሩኲልዮ ሊቀጳጳስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ ኤክቶር ሚገል ካብረኾስ ቪዳርተ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ትኵረት ሰጥተው መግለጫ ሲሰጡ እንደገለጡት፡ የፐሩ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት የፐሩ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የሐዋርያ ጴጥሮስ ወኪል ከሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያላትን አንድነት ለመግለጽ ሆኖ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የእምነት ሐዋርያነት የሚያንጸባርቅ ጉብኝት ነው። አያይዘው የኵላዊት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መሪ ከሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚለገሥልን አባታዊ ምክር ለማዳመጥ እና በአጠቃላይ የኵላዊት ቤተክርስትያን በተለይ የፐሩዋን ሁኔታ በተመለከተ ለመወያየት እና ለመምከር መሆኑ አስገንዝበዋል።

በፐሩ የትሩኲልዮ ሊቀጳጳስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር ብፁዕ አቡነ ኤክቶር ሚገል ካብረኾስ ቪዳርተ የፐሩ ቤተክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ ሲገልጹ፡ ቤተክርስትያኒቱ የስብከተ ቅዱስ ወንጌል ተልእኮ እያቃናች፡ ሀገሪቱ ውስጥ ያንሰራፋው ድኽነት ለመቀነስ በመጣጣር ላይ ትገኛለች።

ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ቀውስ እና የላቲን አመሪካ ሀገራት ግላዊ ችግር ተንተርሶ በመስፋፋት ላይ ያለውን ድኽነት ለመግታት የፐሩ ቤተክርስትያን፡ ማሕበራዊ ትምህርተ ቤተክርስትያን ላይ በመመርኰስ አቅምዋ በፈቀደው እየተንቀሳቀሰች መሆንዋ ብፁዕ አቡነ ኤክቶር ሚገል ካብረኾስ ቪዳርተ አስገንዝበዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.