2009-05-06 12:07:23

የአብሩዞው የመሬት መናወጥ አደጋ


በአብሩዞ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረው የመሬት መናወጥ አደጋ ሳቢያ ቤቱንና ንብረቱን በማጣት በመጠለያ ዱንኳን የሚገኘው የክልሉ ሕዝብ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሚሆንና በተለይ ደግሞ የክልሉ ዳግመ ግንባታ ተጠናቆ ተፈናቃዩ ሕዝብ ወደ ቤቱ የሚመለስበት እቅድ እግብ ለማድረስ አመታት ሊፈጅ እንደሚችልም ተሰግተዋል፣ እንዲህ ከሆነ የዚሁ እህዝብ በግዚያዊ መጠለያ የመቆየቱ ገደብ ረዥም ሊሆንበት እንድሚችልም ተፈርተዋል፣ ይህ 300 የክልሉ ሕዝብ ለሞት የዳረገው አሰቃቂው የመሬት መናወጥ አደጋ አማካኝነት ከወደሙትና መጠነኛ የመፍረስ አደጋ ከደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 54% ብቻ ማለትም 22,700 መኖሪያ ቤቶች ዳግም ላገልግሎት ሊውሉ እንደሚችሉ የያስቸኳይ የተፈጥሮ አደጋ ተቆጣጣሪ ቢሮ አስታውቀዋል።

በዚሁ ክልል ለተጐዳው ሕዝብ የሚሰጠው የስነ አእምሮ ድጋፍ የሚመሩት የስነ አእምሮ ሊቅ አንቶኒዮ ፒቻኖ፣ ሕዝቡ ተስፋ በማድረግ ዳግመ ግንባታው ተጠናቆ ለማየት ያለው ጉጉት ከፍተኛ ሆኖ እያለ ነገር ግን ይህ እቅድ በተሎ የሚጠናቀቅ ለለ ማይመስልም ሕዝቡ ባጋጠመው አደጋ ሳቢያ የደረሰበትን የስነ አእምሮ ጭንቀት እንደሚያከብደው ነው ካሉ በኋላ አክለውም ከዚህ የአእምሮ ጭንቀት ለማላቀቅ የስነ አእምሮ ሓኪሞች ድጋፍ እየሰጡ ናቸው፣ ሆኖም ግን ይህ ድጋፍ ለብቻው መፍትሔ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

ሁሉን ስታጣ እለታዊ ኑሮህንም ጭምር እንዴት እንደምትመራው ጭምር ነው ግራ የሚጋባው ስለዚህ ከሌሎች ጋር የመገናኘቱ ፍላጐት እየጐደለ በራስ ውስጥ ተዘግቶ የመቅረቱ ምርጫ ያስከትላል እየታየም ነው፣ ስለዚህ የተጎዳው ሕዝብ ከደረሰበት የአእምሮ ጭንቀት ለማላቀቅ ስነ አእምሮአዊ ብቻ ሳይሆን የተሟላ ቁሳዊ ድጋፍ መስጠት ወሳኝ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.