2009-05-06 14:20:26

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ቃ. ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺ የሚገመቱ ምእመናን ነጋዲያን ያየተለመደውን የዕለት ረቡዕ ሳምንታዊው አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ቅ.ዮሐንስ ዳማሲን በተባለው የምስራቅ ክርስትና ጸሐፊና የነገረ መልኮት ሊቅ ላይ ያነጣጠረ ሰፊ አስተምህሮ ያቀረቡት በጣልያንኛ ቋንቋ ሲሆን ለሌላው ቋንቋ ተናጋሪዎችም አጭር አስተምህሮዎች አድርገዋል።

ክቡራትና ክቡራን አድማጮቻችን ቅ.አ.ር.ሊ.ቃ. ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ለእንግሊዚኛው ቋንቋ ተናጋሪዎች ያሰሙት አስተምህሮ ትርጉም እንደሚከተል ነው።

ውድ ውንድሞቼና እኅቶቼ፣ ቅ.ዮሓንስ ዳማሲን በምሥራቁ ተዮሎጊ ታሪክ ከፍተኛ ታዋቂነት ያለው ሊቅ ትልቅ ቅዱስ ነው።

ትውልድ አገሩ ሶሪያ በአረቦች አገዛዝ ሥር በነበርችበት ዘመን እጅግ ሃብታምና ባለጸጋ ከነበሩት ክርስትያን ቤተሰብ ተወለደ፣ የገዳም ሕይወት ለመኖር በመፈለጉም ትልቅ የመሻሻልና የእድገት ተስፋ የሚታይበት የነበረ የሞያ ሥራውን ተወ፣ የቅ.ዮሐንስ ዳማሲን ታዋቂ ሥራዎች ፀረ ቅዱሳን ምስሎች በተነሳው ባህል አንጻር ያቀረባቸው ንግግሮችና ጽሑፎች ናቸው፣ እነዚህ ጽሑፎች የቅዱሳን ምስሎች አክብሮት በሚመለከት ተገቢ ተዮሎጋዊ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጣሉ።

ቅ.ዮሐንስ ዳማሲን ለመጀመሪያ ጊዜ ለእግዚኣብሔር ብቻ በሚሰጠው ስግደትና ክርስትያን ምስሉ የሚወክለውን ቅዱስ ለማስተንተን በሚጠቀምበት ምስል አክብሮት መካከል ያለውን ልዩነት ካሳዩት ሰዎች አንድ ነበር።

አዎ እውነት ነው፣ በብሉይ ኪዳን ቅዱስ ምስሎች በጥብቅ የተከለከሉ ነበር፡ ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ሥጋ በመልበሱ በኢየሱስ ግዙፍ የሚታይ ነገር ሆኖአል፡ በዚህ ምሥጢር አሁን ቁስ አካል ወይም ግዙፍ ነገር አዲስ ክብርና ማእረግ አግኝቶአል፣ ዕፀ መስቀል፡ የወንጌል መጽሐፍ እንዲሁም የመሰዊያ ታቦት ሁላቸው እግዚአብሔር ድኅነታችንን ለማምጣት የተጠቀመባቸው ነገሮች ናቸው፣ ስለዚህ አሁን ቁስ አካል ወይም ግዙፍ ነገር ከእግዚብሔር ጋር ያለን ግኑኝነት ምሥጢር ምልክት ሆኖ ያገለግላል።

በቅዱሳት ምሥጢራት ስንሳተፍ፡ የቅዱሳን ምስሎች ስናከብር በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በእምነት የምናደርገው ከሆነ በእውነት የጸጋ ምንጭ ይሆናሉ፣ ምንም እንኳ ሰው ኃጢአተኛ ቢሆንም ቅሉ እግዚብሔር መጨረሻ የሌለው ደግነቱና ቅድስናው እንዲሳተፉ በመቀደስ በወንዶችና በሴቶች ውስጥ እንዲኖር መርጦአል ብሎ ይጽፍ ነበር ካሉ በኋላ ቅ.አ.ር.ሊ.ቃ. ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ይህንን እኛ ዘንድ ለመኖር የፈቀደውን አምላክ በደስታ ልቦቻችን ከፍተን እንቀበለው ሲሉ አሳስበው በጉባኤ አስተምህሮው ለተሳተፉት ሁሉ ሰላምታና ሐዋርያዊ ቡራኬ በማቅረብ ለዕለቱ ያሉትን ትምሀርተ ክርስቶስ ፈጽመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.