2009-05-06 12:11:21

ዓመታዊ ስለ እናቶችና ሕፃናት ጉዳይ የሚገመግም ሰነድ


ሰቭ ዘ ቺልድረን የተስየመው የሕፃናት አድን ድርጅት ስለ እናቶችና ሕፃናት ጉዳይ የሚገመግም ዓመታዊ ሰነድ ማቅረቡ ሲነገር፣ ከዚህ ሰነድ ለመረዳት እንደተቻለውም፣ ለእናቶችና ለሕፃናት አቢይና የተዋጣለት እንክብካቤ የሚያደርጉ አገሮች፣ በቅድሚያ ኖርዌይ ቀጥላም አውስትራሊያና እናቶችና ሕፃናት በጣም ለችግር ተጋልጠው የሚገኙባቸው አገሮች ደግሞ፣ ኒጀር ሰራሊዮንና ቻድ መሆናቸው ታውቀዋል።

ይህ የሕፃናት አድን ድርጅት መሠረታዊ ሕክምና ትምህርት ሥራና ራስን ለመቻል የሚያግዝ የኤክኖሚ አቅም መመዘኛ መሠረት በማድረግ፣ ባለማችን ስለ እናቶችና ሕፃናት ጉዳይ የሚገመገመው ሰነድ እንደሚያመለክተውም በበለጸጉት አገሮች እየተሻሻለ በድኾች አገሮች በጣም እያሽቆለቆለ መምጣቱ ሲታወቅ፣ ባለማችን አሁንም 500 ሺሕ ሴቶች በእርግዝና በሚያጋጥመው የጤና መታወክ ሳቢያ በያመቱ የሞት አደጋ እንደሚያጋጥማቸውና 9 ሚሊዮን ሕፃናት ገና 5 ዓመት እድሜ ሳይሞላቸው ከዚህ ዓለም በሞት እንደሚለዩ ሰነዱ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.