2009-05-06 12:00:10

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እስራኤልን ይጐበኛሉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 8 ቀን እስከ ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅድስት መሬት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ቀደም ተበሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ ክልል ሕዝብ ቅዱስ አባታችንን ለመቀበል በመዘጋጀት ላይ መሆኑ በእስራኤል የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ፍራንኮና የእየሩሳሌልም የላቲን ሥርዓት ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉዓድ ጥዋል ትላትና ከሰጡት ጋዜጣዊ መገልጫ ለመረዳት ተችለዋል።

ብፁዓን ጳጳሳቱ የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉዞ የተዋጣለት እንዲሆን በመደረግ ላይ ያለው ቅድመ ዝግጅት ለጋዜጠኞች ሲያሳውቁ፣ የጋዜጠኞች ተልእኮና ኅላፊነት እግምት ውስጥ በማስገባት የዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ዓላማ የጸሎት የእምነት ጉዞና እንዲሁም በዚህ ክልል አንድነትና ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ይፋ እንዲያደርጉ አደራ እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።

በእስራኤልና በፍልስጥኤም ባለው የወቅቱ የተወሳሰበው ሁኔታ አማካኝነት የቅዱስ አባታችን የቅድስት መሬቱ ሐዋርያዊ ጉብኝት ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው ጥንቃቄ የሚያሸው ጉዳይ ነው፣ ስለዚህ ጉብኝቱ ሰላምንና አንድነት እምነትን የሚያነቃቃ ነው በማለት ብፁዕ አቡነ ጥዋል አስታውቀዋል። ይህ እየሩሳሌም በሚገኘው የኖትሬ ዳም ማእከል በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚያመለክተውም፣ ጉብኝቱ በብዙ የመገናኛ ብዙሃን የተዘነጋው በቤተልሔም አቅራቢይ የሚገኘው የፍልስጥኤማውያን ተፈናቃዮች መጠለያ እንደሚጎበኙና በቤተልሔም ለ 250 ክርስትያን ፍልስጥኤማውያን መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያቀርቡም ከገለጡ በኋላ፣ በቺስጆርዳኒያ ለ 15 ሺህ ክርስትያን ፍልስጥኤማውያንና ንግግር እንድሚያሰሙ፤ ያድ ቫሸም በአሁዳውያን ላይ የተፈጸመው እልቂት መታሰቢያን እንደሚጐበኙና በዮርዳንስ ስለ ቤተ ክርስትያን በናዝሬት ስለ ሕይወት በእየሩሳሌል ስለ ሰላምና እርቅ በቤተልሔም ደግሞ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚያበክር መሆኑም ብፁዕ አቡነ ማርኩዞ ለጋዜጠኞች ይፋ አድርገዋል።

በመጨረሻም ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ፍራንኮ እንደገለጡትም፣ ቅዱስ አባታችን ቅዱሳት ሥፍራን በመጎብኘት እሁድ እኩለ ቀን ማርያማዊ ጸሎት በማሳረግ፣ የቅድስት መሬት ክርስትያኖችን እንደሚባርኩና እንድሚያበረታቱ ከገለጡ በኋላ ባጠቃላይ ጉብኝቱ ውይይትና እርቅ እውን እንዲሆን ሰላምን የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.