2009-05-04 13:04:15

የክርስትያን ማህበረሰብ ብሔራዊ ጉባኤ


የዴሞክራሲያዊት ሬፑብሊክ ኮንጎ ክርስትያን ማኅበረሰብ ብሔራዊ የሰላም ጉባኤው ዛሬ መጀመሩ ሲገለጥ፣ በዚህ በሚካሄደው ጉባኤ ባገሪቱ ከሚገኙት ከተለያዩ ሰበካዎችና ቁምስናዎች የተወጣጡ ልኡካንና የተለያዩ የክርስትያን ማኅበራት ተጠሪዎች እየተሳተፉ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል። ይህ የሚካሄደው ጉባኤ ባገሪቱ ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ፣ ብቃት ያላቸው ቅን ያመራር አካላት ለማበረታታትና በዚህች በዴሞክራሲው ጎዳና በምትገኘው አገር ያለቸው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ሰላም ፍትሕና ደህንነት እንንዲረጋገጥ ምን ማድረግ ይኖርባታል በሚሉት የጥያቄ ርእሶች በመወያየት ምላሽ ለመስጠት ጥረት እንደሚያደርግ ሲገለጥ፣ እንዲሁም ባገሪቱ እ.ኤ.አ. በ 2011 ዓ.ም. የሚካሄደው ምርጫ የተዋጣለት ለማድረግ ምን መደረግ አለበት ከሚለው መንፈስ በመነሳሳት የመምረጥና የመመረጥ መብት ምን ማለት መሆኑ በጉባኤው ሰፊ አስተምህሮ እንደሚሰጥም ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.