2009-05-04 13:09:38

የሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎች


በሶማሊያ የባህር ክልል የሚንቀሳቀሱትን የውጭ አገር መርከቦችን ለማገት የተሰማሩት የሶማሊያ የባህር ወንበዴዎች ሴራ ገና አለመገታቱ ሲነገር፣ ንብረትነቷ የፓኪስታን የሆነቸው የጭነት መርከብ መጥለፋቸውና መርከቧን ነጻ ለማስለቀቅ ድርድር እየተከናወነም ሲሆን፣ ከትላትና በስትያ እንዲት የተባበሩት መንግሥታት ሥራ ማስፈጸሚያ ቁሳቁስና እንዲሁም የምግብ እርዳታ የጫነች የኡክራይ መርከብ ማገታቸውም ተገልጠዋል። ይህ በንዲህ እንዳለም ለኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፍራንኮ ፍራቲኒ ልዩ ልኡክ ማርገሪታ ቦኒቨር በሶማሊያ ያካሄዱት ጉብኝት ማጠናቀቃቸውና እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 11 ቀን 2009 ዓ.ም. የተጠለፈችው በጠቅላላ 16 ባህረኞች ከነዚህም ውስጥ አሥር የኢጣሊያ ዜጎች የሚገኙባት የንግድ መርከብ ነጻ ለማስለቀቅ ያካሄዱት ውይይት እንዳረካቸውም ጉብኝቱን እንዳጠናቀቁ መግለጣቸው ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.