2009-05-04 12:47:01

የሮማ ሰበካ የጤና ጥበቃ የሐዋርያዊ አገልግሎት ባለ ሙያዎች


የሮማ ሰበካ በጤና ጥበቃ ዘርፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚሰጡት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች በቅድስት መሬት መንፈሳዊ ንግደት እያከናወኑ መሆናቸው ተገለጠ። እነዚህ በጤና ጥበቃው ረገድ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚሰጡት የሮማ ሰበካ ልኡካን በዚህ በሚያካሂዱት መንፈሳዊ ንግደት በቅድስት መሬት በጤና ጥበቃው መስክ ሓዋርያዊ አገልግሎት ለሚሰጡትና በተለያዩ ሕክምና መስጫ ማእከሎች በመንፈሳዊ መሪነት አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ ካህናት የተሓድሶ ህንጸት እንደሚሰጡ ለማወቅ ሲቻል፣ ተልእኮውን የመሩት የሮማ ሰበካ የጤና ጉዳይ የሚከታተለው ሓዋርያዊ ድርገት ተጠሪ ብፁዕ አቡነ አርማንዶ ብራምቢላ ስለ ሓዋሪያዊ ጉብኝቱ በማስመልከት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው በቅድሚያ የክርስትና መሠረት የሆኑትን ሥፍራዎችን በመጎብኘት እምነትን ለማደስ የሚከናወን መሆኑ አብራርተው በሌላው ረገድ በዚሁ ክልል በጤና ጥበቃው ዘርፍ ተሰማርተው ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሚስጡት ሁሉ ለማበረታታትና አስፈላጊ ያስቸኳይ ሕንጸት ለመስጠት ያቀደ ነው ካሉ በኋላ አክለውም የመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረሰብ ቅድሱ አባታችንን ለመቀበል በመዘጋጀት ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሚከናወን በመሆኑም አጋጣሚው ጉብኝቱን ለየት እንደሚያደረገውም አስታውሰው እምነትን በማደስ እምነት የሚመሰክር ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚያነቃቃ ነው እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.