2009-05-04 14:22:11

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ የፖላንድ ጉብኝታቸው ፈጽመዋል፡


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ የፖላንድ ጉብኝት መፈጸማቸው ተነግረዋል። ብፅዕነታቸው ፖላንድን ለአራት ቀናት የጐበኙ ሲሆን ከተለያዩ የሀገሪቱ ቤተክርስትያን ባላሥልጣናት ጋር መገናኘታቸው ተገልጠዋል።

ከፖላንድ ከመነሣታቸው በፊትም በገዳመ ማርያም በዠዝና ጎራ በርካታ ጳጳሳት ካህናት ደናግል እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ባሰሙት ስብከት ቅዱስ ስፍራው፡ የፖላንድ ናዝሬት ተብሎ ለመጠራት የሚችል ቅዱስ ስፍራ መሆኑ ጠቅሰው፡ እዚህ የሚሰበሰቡ ምእመናን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው ማለታቸው እና ቅድስት ድንግል ማርያም ናዝሬት ላይ፡ ኢየሱስን ለዓለም ያስተዋወቀችበት ቦታ ነው ሲሉ መግለጣቸው ተመልከተ።

ገዳመ ማርያም ዠዝና ጎራ ከወላዲተ አምላኽ ጋር የምትጸልይበት እና መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ዓለምን እንዲፈውስ የሚጸለይበት ቦታ መሆኑንም ገልጠዋል።

ገዳመ ማርያም ዣዝና ጎራ እና የፓኦሊኒ አባቶች የተሳሰሩ መሆናቸው ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ጠቅስው፡ ማኅበራቸው ጳጳሳዊ እውቅና ያገኘበትን ሰባት መቶኛ ዓመት በማክበር ላይ እንዳሉ በማመልከት፡ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.