2009-05-04 13:02:17

በሕንድ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ


በሕንድ የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ብሔርተኝነትንና የተለያዩ አናሳ ሃይማኖቶችን በሚቃወም ፖሊቲካዊ ቅስቀሳ የተሸኘ መሆኑ ሲገለጥ፣ አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ተከታዮች በድረ ገጻቸው ያገሪቱን አናሳው የክርስትያንና የምስልምና እምነት ተከታዮችንና እነዚህን ሃይማኖቶችን የሚያንቋሽሹ መልእክቶች እያሰራጩ መሆናቸው የህንድ የክርስትያን እንቅስቃሴና የክርስትያን ማኅበራት የሰጡትን መገልጫ በመጥቀስ ፊደስ የዜና አገልግሎት በሰጠው የዜና ምንጭ አስታውቀዋል።

እነዚህ ሂንዱ አክራርያን፣ መላይቱ ህንድ ክርስትያን ወይንም እስላም አገር ከመሆንና የሂንዱ ሃይማኖት ምእመናን አናሳ ያገሪቱ ማኅበረሰብ ክፍል እንዳይሆኑ ህንድ የሂንዱ ሃይማኖት ተከታይ ሕዝብ አገር ለማድረግ የሚጥሩና ይኸንን ርእዮት ለሚያነቃቁ የፖሊቲካ ሰልፎችን ምረጡ የሚል መፈክራዊ ጥሪዎች በድረ ገጻቸው እያስተጋቡ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ያገሪቱ የክርስትያን እንቅስቃሴዎችና ማኅበራት የሂንዱ አክራርያን ምእመናን እያካሄዱት ያለው ጸረ ክርስትያን ዘመቻ ጥላቻና ቂምን ከሚያስተጋባው በኦሪሳ ክልል ለብዙ ክርስትያን ምእመናን ለሞትና ላደጋ ብሎም ለመፈናቀል አደጋ ካጋለጠው የሂንዱ አክራሪያ ካረማመዱት የፖለቲካ ርእዮት የመነጨ መሠረት የሌለው ነው በማለት ምላሽ እንደሰጠበትም የዜናው አገልግሎት በማስታወቅ፣ ያገሪቱ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ማንኛውም የመምረጥ መብት ያለው ያገሪቱ ዜጋ የህሊና ነጻነት በተካነው ሃላፊነት ተመርቶ ሰላምና ወንድማማችነት ይረጋገጥ ዘንድ አልሞ ድምጽ ይሰጥ ዘንድ ጥሪ ማስተላለፏ ፊደስ የዜና አግልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.