2009-05-04 12:41:17

ቅዱሱ አባታችን እሥራኤልን ይጎበኛሉ


ቅዱሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ከግንቦት 8 ቀን 2009 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅድስት መሬት ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ከወዲሁ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ሓዋሪያዊ ጉብኝቱ የተዋጣለት ይሆን ዘንድ ቅድመ ዝግጅቱ በሚያረካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የቅድት መንበር የዜናና የማሕተም ክፍል አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል። ኣባ ሎምባርዲ በሰጡት የርእሰ አንቀጽ መግለጫ፣ ሓዋርያዊ ጉብኝቱ በዮርዳኖስ ኔቦ ተራራ የሚገኘው ለዝክረ ሙሴ የተሰራውን ባሲሊካ በመጎብኝተ ተጀምሮ ቀጥሎም እየሩሳሌም ቤተሌሄምንና ናዝሬትን ያድ ቫሼምን እንዲሁም እዛው የሚገኘውን መስጊድና አንድ የፍልስጥኤም ተፈናቃዮች መኖርያ ክልል የሚያጠቃልል መሆኑ አስታውቀዋል።

ሓዋርያዊ ጉብኝቱ የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ታሪክ የተፈጸመባቸውን የእምነት ቅዱሳት ሥፍራዎችን የሚመለከት መሆኑም ተገልጠዋል። ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ቀጥሎም ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚካሄደውን የጋራው ግኑኝነት በሚያጠናክርና እንዲሁም ካይሁድና ከፍልስጥኤማውያን ጋር ያላውን የወንድማማችነትን መንፈስ በሚያረጋግጥ ሁኔታ መከናወኑ ያስታወሱ አባ ሎምባርዲ አክለውም ቅዱሱ አባታን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ በክልሉ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ የሚደረገው ጥረት የተዳከመ በሚመስልበትና ወቅት የሚከናወን በመሆኑ ሓዋርያዊ ጉብኝቱ በክርስትያኖች መካከል አንድነትን እውን እንዲሆን የሚያነቃቃና የጥላቻ መንፈስ ተወግዶ እርቅና ሰላም እንዲድረጋገጥ የሚገፋፋ ይሆን ዘንድ ቅዱስ አባታችንን በጸሎታችን እንሸኛቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.