2009-05-01 16:30:00

የቱሪዝም ሐዋርያዊ ግብረ-ተልዕኮ፡




ዛሬ ሮማ ውስጥ በቅዱስ ካሊስቶ አዳራሽ የቱሪዝም ሐዋርያዊ ግብረ ተልዕኮ ስብሰባ መጀመሩ ተገልጠዋል። ስብሰባው በቅድስት መንበር የስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት መዘጋጀቱ እና በምክር ቤቱ ሊቀመንበር በሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ሊቀመንበርነት እንደሚመራ ከቦታው የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

የስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ እንደገለጹት፡ ስብሰባው፡ የቱሪዝም ሐዋርያዊ ግብረ ተልዕኮ ቀስቃሽ አቡናት እና ዳይረክተሮች ተሰባስበው በጋራ የወቅቱ የኤውሮጳ የቱሪዝም ሁኔታ ለማጤን መሰረተ አላማ ያለው ነው።

የሌሎች ሀገራት የቱሪዝም ሁኔታ አዋቂዎች እና ልኡካን በዚሁ ስብሰባ ተሳታፊ መሆናቸውም እና ወቅታዊ የቤተክርስትያን ሐዋርያዊ ግብረ ተልዕኮ ሁኔታ በተመለከተ ጥልቅ እና ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ አመልክተዋል።

ቅድስት መንበር እኤአ ከ1952 ዓ.ም. እስካሁን ድረስ የቱሪዝም ሐዋርያዊ ግብረ ተልዕኮ ትኵረት የሰጠ፣ ያላትን ሰነድ እና የተከናወኑ ድርጊቶች በሙሉ በኮምፓክት ዲስክ ተቀርጾ እንደሚቀርብም ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ አስገንዝበዋል።

ብፁዕ አቡነ ማርከቶ እንዳመለከቱት፡ ቤተክርስትያን ቱሪስቶች እና ሀገር ጐብኚዎች በተመለከተ ዐቢይ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምግብራዊ ጥንቃቄ ታደርጋለች፡ አከባቢ ጥበቃ በተመለከተም እንዲሁ፤ በተለይ የእምነት ጥንታውያን አድባራት አብያተክርስትያኖች የሀይማኖት ቅዱሳን ቅርሶች እና ቤተመዘክሮች፡ ለመጐብኘት ብቻ ለሚፈልጉ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የተቻላት ሁሉ እንደምታደርግ ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ፡ የሲቪል የቱሪስት ድርጅቶች እንግዶቻቸው የሃይማኖት ቦታዎች ለመጐብኘት ሲፈልጉ ከየቤተክርስትያኑ የቱሪዝም ጽሕፈት ቤቶች ጋር ግኑኝነት እንደሚያደርጉ ብቻ ሳይሆን መልካም ግንኙነት እንዳለ ጠቅሰው፡ ቱሪዝም የውይይት የመተዋወቅ ባህላዊ ልውውጥ የሚረዳ መሆኑ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የፍትወተሥጋ ቱሪስቶች እየተባሉ የሚጠሩ እና የሚፈጽሙት ሥነ-ምግባር አልባ ድርጊቶች በእጅጉ አሳዛኝ መሆኑ ይህም መገታት እንዳለበት ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ማርከቶ መግለጻቸው ተዝግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.