2009-05-01 16:20:24

የብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የፖላንድ ጉብኝት፡


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ፡ ፖላንድን እየጐበኙ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፡ የሉብሊኖ ዮሐስ ጳውሎስ ዳግማዊ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ብፅዕነታቸውን የሲቭል መብት የክብር ዶክትሬት ማዕርግ መሸለሙ ከዚሁ ቦታ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ከሉብሊኖ ከተማ የመጣ ዜና እንደሚያመለክትው፡ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በሉብሊኖ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዩኒቨርሲቲ ቤተክርስትያን ውስጥ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

በዚሁ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ ‘በዚሁ ብዙ ተስፋ በማይታይባት ዓለም ላይ የክርስትያን እሴቶች ጠበቅ አርጎ መያዝ ያስፈልጋል። ዘመናዊ ኅብረተሰብ ክርስትያናዊ እሴቶችን መዘንጋት ብቻ ሳይሆን ችላ ሲል እንደሚታይ’ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በስብከታቸው ላይ መግለጣቸው ይህ ከሉብሊኖ የመጣ ዜና አስታውቀዋል።

ቤተክርስትያን ክርስትያናዊ እሴቶች እና ባህል ለማስጠበቅ ያለሰለሰ ጥረት እንደምታካሄድ የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፡ ካቶሊካውያን ዩኒቨሲቲዎች የጥረቱ ማዕከል መሆናቸው ማስገንዘባቸው ተመልክተዋል።

በዚሁ ሀያ አንደኛ ምእተ ዓመት የሰው መሠረታዊ ክብር ሲቀነስ እና ሲጣስ እንደሚታይ የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ቤተ ክርስትያን እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ሰው ክብሩ ግርማው እና መብቱ ከመታደግ እንደማትቦዝን ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.