2009-05-01 16:15:11

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የኮሎምብያ ፕረሲዳንት ተቀብለው አነጋገሩ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ የኮሎምብያ መንግሥት መሪ ፕረሲዳንት አልቫሮ ኡሪበ ቨለጽ ተቀብለው ማነጋገርቸው የቅድስት መንበር ማሕተም ክፍል መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የኮሎምብያ መሪ ፕረሲዳንት አልቫሮ ኡሪበ ቨለጽ፡ ኮሎምብያ ውስጥ ጸረ ዕፀ-ፋርስ ለመግታት የሚካሄደው ጥረት ሀጋሪቱ ውስጥ በርካታ ዜጎች ያጠቃው ድኽነት፡ የቤተክርስትያን እና መንግሥት ትብብር ትኵረት የሰጠ ውይይት አካሄደዋል።

ፕረሲዳንት አልቫረጽ ኡሪበ ቨለጽ ቫቲካን ውስጥ ያካሄዱት ውይይት በመቀጠል በቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ሐላፊ ከሊቀጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣችው መገልጫው አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.