2009-04-27 15:57:32

የር.ሊ.ጳ. ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የአረብ ሊግ ዋና ጽሐፊ ውይይት፡


የቫቲካን መግለጫ እንዳመለከተው፡ ባለፈው አርብ ከቀትር በኃላ ቫቲካን ውስጥ በር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ እና የአረብ ሊግ ዋና ጽሐፊ አምር ሙሳ መሀከል የተደረገው ውይይት የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ እና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ትኩረት የሰጠ ነበር።

ቅድስት መንበር እና የአረብ ሊግ የመረዳዳት መዘክር መፈራረማቸው እና መዘክሩ በቅድስት መነበር የውጭ ጉዳይ ዋና ሐላፊ በሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማመበርቲ እና በዋና ጽሐፊ አምር ሙሳ መፈረሙ መግለጫው አስታውሰዋል።

በዚሁ መግለጫ መሰረት ቅድስት መንበር እና የአረብ ሀገራት ማሕበር ለሰላም እና ፍትህ በጋራ ለመስራት ተግባብተዋል።

የእስራኤል እና ፍሊስጢኤም የቆየ ግጭት በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንድያገኝ ሁለቱ ወገኖች በጋራ ለመስራት ማቀዳቸውንም መግለጫው አክሎ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.