2009-04-27 15:47:55

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ለቅዱስ ጳውሎስ ዓመት መዝግያ ክብረ በዓል የሚወክልዋቸው ሰባት ካርዲናሎች ጠቍመዋል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ የሐዋርያ ጳውሎስ ዓመት መዝጊያ፣ ፊታችን ሰነ ወር 29 ቀን በተለያዩ የዓለም አከባቢዎች በሚካሄደው ክብረ በዓል የሚሳተፉ ሰባት ካርዲናሎች መጠቈማቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

በቅድስት መንበር የክርስትያን አንድነት ጳጳሳዊ ሊቀመንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር ወደ ቅድስት ከተማ ኢየሩሳሌም እንደሚጓዙ፡ በቅድስት መንበር የቤተሰብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤንዮ አንቶነሊ ወደ ሞልታ እንዲሁም፡ የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ብፁዕ ካርዲናል ረናቶ ራፋኤለ ማርቲኖ ወደ ቆጵሮስ እንደሚጓዙ ፣ የውስጠ ሃይማኖት ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ብጹዕ ካርዲናል ጂን ሉዊስ ቱራን ወደ ቱርክ እንደሚያመሩ ያመለከተ፣ የቫቲካን መግለጫ አይያዞ የቀድሞ የስብከተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት የበላይ ሀላፊ ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ቶምኮ ወደ ግሪክ በእስፓኛ የማድሪድ ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ማሪያ ሮኾ ወደ ሲርያ እንደሚጓዙ በፈረንሳ የፓሪስ ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ትሮይስ ወደ ሊባኖስ እንደሚጓዙ መግለጫው አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአየርላንድ ደሪ ከተማ ላይ የሎንግ-ታወር ቤተክርስትያን የተመሰረተችበት መቶኛ ዓመት ፊታችን ሰነ ወር ላይ ዘጠኝ ቀን እንደሚከበር እና የቅዱሳን እንድርያስ እና ኤዲንበርግ ቤተክርስትያን ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ከይት ማይክል ፓትሪክ ኦብራያን በዚሁ በዓል ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አሥራ ስድሰተኛን እንዲወክሉ መጠቈማቸው ተያይዞ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.