2009-04-24 16:26:10

ጉባኤ ጸረ የዘር-አድልዎ


በስዊጸርላንድ ጀነቭ ላይ ሲካሄድ የሰነበተው ጸረ-ዘር አድልዎ አለም አቀፍ ጉባኤ መጠናቀቁ ከቦታው ተነግረዋል፡ ጉባኤው በአጠቃላይ፡ የዘርም ሆነ ሌሎች የሚፈጸሙ አድልዎዎች በአንድ ድምጽ ማውገዙ ተመልክተዋል።

በስዊትጸርላንድ በሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋሞች የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲላቫኖ ማሪያ ቶማሲ፣ በዚሁ አለም አቀፍ ጸረ-የዘር አድልዎ የተካሄደ ጉባኤ የተገኙ ሲሆን፡ ከስምንት አመታት በፊት በደቡባዊ አፍሪቃ ዱርባን ላይ ጸረ-የዘር አድልዎ የተካሄደ አለም አቀፍ ጉባኤ አስታውሰው የዘር አድልዎ ተገታ ለማለት ባይቻልም የጀነቩ ጉባኤ አዎንታዊ መኖሩ መግለጣቸው ተገልጠዋል።

ቅድስት መንበር በማንኛውም መልኩ የዘር አድልዎ እንዲገታ እንደምትሻ የገለጹ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ በተለያዩ ቦታዎች በእምነታቸው የተነሣ የሚጕላሉ ሰዎች እንዳሉ፣ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ አድልዎ ሲደረግ እንደሚታይ ማስገንዘባቸው ተነግረዋል።

ጸረ-ወሊድ፡ ጽንስ ማስውረድ ራሱ ለሰው ሕይወት መንፈግ ስለሆነ አስከፊ ተግባር መሆኑ ጀነቭ ላይ በሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ መግለጣቸው ተያይዞ ተነግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.