2009-04-24 16:38:22

የጣልያን መንግሥት በመሬት ለተጐዳ ክልል ስምንት ሚልያርድ ዝግጁ ማድረጉ አስታውቀ

 


የጣልያን መንግስት በመካከለኛው የሀገሪቱ ክልል በዚሁ ወር መጀመርያ ሳምንት በመሬት መናወጥ የወደሙ የአብሩጾ ከፍለ ሀገሮች ከተሞች ዳግም ለመገንባት ስምንት ሚልያርድ ዩውሮ ዝግጁ ማድረጉ የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አስታውቀዋል።

የጣልያን መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ፡ በደቡባዊ ጣልያን በደሴት ሳርደኛ ማዳለና ላይ እንዲካሄድ የታቀደው የቡድን ስምንት ጉባኤ በአብሩዞ ላ”ኲላ ከተማ ላይ እንዲከናወን የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑ ማስገንዘባቸው ተነግረዋል።

ላ”ኲላ ከተማ በመሬት መናወጥ በኃይል ከተጐዱ ከተሞች አንድ መሆንዋ የሚታወስ ነው ፡

የቡድን ስምንት ጉባኤ በዚሁ ክልል ማለት በላ”ኲላ ከተማ እንዲካሄ የተፈለገው መንግስት በመሬት ነውጥ ከተሰቃየ ህዝብ ጐን መቆሙ እና ለማሳየት ተስፋ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጣቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.