2009-04-24 16:06:33

የቅድስት መንበር እና አረብ ሊግ መሞራንደም


የቅድስት መንበር እና የአረብ ሊግ ሀገራት ቫቲካን ውስጥ በጋራ ለመሥራት የመግባባት መዘክር መፈራረማቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል። ለቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ሲፈርሙ፣ ለአረብ ሊግ ደግሞ፡ የአረብ ሀገራት ማሕበር ዋና ጽሐፊ አምር ሙሳ መፈረማቸው መግለጫው አስገንዝበዋል።

በዚሁ የመግባባት ሥርዓተ መዘክር በቅድስት መንበር በኩል፡ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ጨምሮ በርካታ ጳጳሳት መገኘታቸው፣ በአረብ ሊግ በኩል ደግሞ በቅድስት መንበር የአረብ ሀገራት ልኡካን ቡድን ዋና ሐላፊ ዋሊድ አል ጋርጋኒ በኤውሮጳ የአረብ ሀገራት ጉዳይ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዲና ዱአይ እና በከፊል በቅድስት መንበር የአረብ ሀገራት አምባሳደራት መገኘታቸው መግለጫው አስታውቀዋል።

የቅድስት መንበር መግለጫ እንደገለጠው፡ ስምምነቱ ቅድስት መንበር እና የአረብ ሀገራት በፖሊቲካ እና ባህላዊ ዘርፎች በኩል በተጠናከረ መልኩ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸው ስምምነት ነው።

ስምምነቱ በክልል እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሰላም እና መረጋጋት እንዲገኝ በጋራ ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እና የውስጠ ሀይማኖት ውይይት ለማካሄድም አጋዥ መሆኑ ተያይዞ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.