2009-04-22 15:27:09

ጀነቭ: ቅድስት መንበር እና ኢራን


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በስዊዘርላንድ ጀነቭ ላይ የዘር አድልዎ ትኩረት የሰጠ አገሮች አቀፍ ጉባኤ እየተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በትርምስ የተሸኘ ጉባኤ እየሆነ መምጣቱ ከቦታው የተገኙ ዜናዎች ያመለክታሉ።

ይህ የሆነበት ምክንያት የኢስላም ረፓብሊክ ኢራን መራሔ መንግሥት ፕረሲዳንት አህመዲን ነጃድ፣ በዚሁ የጀነቭ ጉባኤ ተገኝተው እስራኤልን በዘረኝነት በመወንጀላቸው የተነሣ ከየኤውሮጳ ኅብረት ወቅታዊ ሊቀመንበር ቸክ ረፓብሊክ በስተቀር የኅብረቱ የመንግሥታት ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ጉባኤው ጥለው እንደወጡ ዜናዎቹ አስታውቀዋል።

የኢስላም ረፓብሊክ ኢራን መሪ ፕረሲዳንት አህመዲን ነጃድ በዚሁ ጀነቭ ላይ በመካሄድ ላይ ያለው የዘር አድልዎ የተመልከተ አገሮች አቀፍ ጉባኤ ተገኝተው እስራኤልን በዘር አድልዎ መወንጀል በተያዙበት ግዜ፣ ጉባኤው ጥለው ከወጡ የመንግሥታት ልኡካን በከፊል፣ የዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል ካናዳ አውስትራልያ ጀርመን ኒውዚላንድ እንደሚገኙባቸው ተገልጠዋል ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ጉባኤው በመተራመሱ የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጠው የዘር አድልዎ ለመግታት የሀገራቱ ትብብር እንደሚያሻ መጠየቃቸው ተመልክተዋል ።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ኮሚስዮን ነቪ ፒለይ የኢራን መሪ ፕረሲዳንት አህመዲን ነጃድ ያላቸውን አሉታዊ ተቋም በጋራ ጠንካራ መልስ መስጠት እንጂ ጉባኤውን ጥሎ መወጣት ፋይዳ ቢስ መሆኑ መግለጫ መስጠታቸው ተነግረዋል።

ይሁን እና በየኢራኑ መሪ አህመዲን ነጃድ አመለካከት ምዕራባውያን ሀገራት ቢሆን ሆሎካውስት ናዚ ጀርመን በአይሁድ ላይ ፈጸሙት የተባለው ህልቂት ዘረኛ የእስራኤል መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ ለማስፈር የተጠቀሙበት ዘዴ ነው።

ራሱ ሆሎካውስት ህልቀተ/አይሁድ መኖሩ እንደማያምኑ ፕረሲዳንት አህመዲን ነጃድ እንደሚገልጡም ተያይዞ የደረሰ ዜና አስታውቀዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የተወቀሱ እና የተተቹ አህመዲነጃድ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ

ሲሆን ይባስ ብሎም፡ የኢራን ዕለታዊ ጋዜጣ በዛሬ ርእሰ አንቀጹ እንዳሰፈረው ፕረሲዳንት አህመዲን ነጃድ ጀነቭ ላይ ፍትሕ በመጠየቃቸው ዘረኞች ኤውሮጳውያን አስቆጥተዋል ብሎ ማለቱ ተዘግበዋል ።

የእስራኤል መንግሥት ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎች የኢራኑ መሪ አስተሳሰብ እና ለጉባኤው ያደረጉት ንግግር አጥብቀው መኰነናቸው ተገልጠዋል። ይሁን እንጂ የጀነቩ ጉባኤ እየቀጠለ መሆኑ እና እስከ ፊታችን ዓርብ እንደሚዘልቅ ተመልክተዋል።

የቅድስት መንበር የልዑካን ቡድን በዚሁ የጀነቭ ጉባኤ ተሳታፊ መሆኑ ይታወቃል፣ በድርጅቱ ተቋሞች የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ እንደገለጹት ቅድስት መንበር የዘር አድልዎ ለመግታት በሚካሄዱ ሰላማውያን ድርጊቶች ተሳታፊ መሆንዋ መግለጣቸው ተነግረዋል።

ቅድስት መንበር ትናንትና የሰጠቸው መግለጫ እንዳመለከተው ጉባኤው የፖሊትካ አቋም መግለጫ እና ሌሎች ሀገራት የመዝለፍ መናርያ መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል፡ ጉባኤው ለሰላማዊ ውይይት የማይጋብዝ ጠብ ጫሪ አቋም መገታት እንደሚኖርበት የቅድስት መንብር መግለጫ አክሎ አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.