2009-04-20 18:20:01

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት በአብሩጾ ክፍለ ሃገር


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራስድስተኛ በዚሁ በተያዝነው ሚያዝያ ወር 28 ቀን እኤአ በመካከለኛው ጣልያን በመሬት ነውጥ የተመታውን አከባቢ እንደሚጐበኙ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ መሰረት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ወደ አብሩዞ ክፍለ ሀገር ተጉዘው በመሬት መናወጥ የፈራረሱ አከባቢዎች ኦና እና ላ”ኲላ ከተሞች ይጐበኛሉ በዚሁ ሰበብ ተፈናቅለው በተንዳዎች ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ይገናኛሉ።

በመሬት ነውጥ ምክንያት ለአቢይ ችግር የተጋለጡ ሰዎች ርዳታ በመሰጠት ላይ ከሚገኙ የመንግስት እና የግል የርዳታ ተቋሞች ሰራተኞች ጋርም እንደሚገኛኙ የቅድስት መነበር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል።

በላ”ኲላ ከተማ በኮለማጅዮ ካተድራል ፣ የሕሊና ጸለት እንደሚያደርጉ ቃል አቃባዩ አስታውቀዋል።

የኮለማጅዮ ካተድራል በመሬት ነውጡ ፍጹም ከፈራረሱ ቦታዎች አንዲት መሆንዋ የሚታወቅ ነው።

የላ”ኲላ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጁሰፐ ሞሊናሪ የርሊጳ በነዲክቶስ በመሬት መናወጥ ምክንያት በተመቱ ክልሎች የሚያደርጉት ጉብኝት የእ/ር ስጦታ እና ተስፋ ሰጪ ስለሆነ ህዝቡ በጉጉት እየተጠባበቀ መሆኑ መግለጣቸው ተመልክተዋል።

በመካከለኛው ጣልያን በዚሁ በተያዝነው ወር መጀመርያ ሳምንት በተከሰተው የመሬት መናወጥ፣ 298 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ ፣ ከአንድ ሺ በላይ ቀላል እና ከባድ መቁሰልት እንደደረሰባቸው ከ50 ሺ ህዝብ መጠለያ አልባ መቅረቱ የሚታወስ ነው።

በሌላ በኩል ይሁ እና የኤውሮጳ ሕብረት ኮሚስዮን ለዚሁ ክልል ዳግመ ግንባታ 500 መቶ ሚልዮን ዩውሮ ዝግጁ ማድረጉ ተገልጠዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ፣ የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት በትናንትና ዕለት ሚያዝያ 19 ቀን እንደ ኤውሮጳ አቆጣጠር፣ በገሀግር አቀፍ ድረጃ በሀገሪቱ አብያተክርስትያናት በመሬት ነውጥ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሰዎች ለመርዳት የገንዘብ መዋጮ ዘመቻ ማካሄዱ ታውቆዋል።

በአብያተ-ክርስትያናቱ ተዋጥቶ የተገኘው ገንዘብ ለብሔራዊ ካሪታስ እንደሚሰጥ እና በዚህ ተቋም በኩል በመሬት መናወጡ ለአቢይ ችግር የተጋለጠው ህዝብ እንደሚሰ የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት መግለጫ አስታውቀዋል።

እንደሚታወቀው የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ቀደም ሲል አምስት ሚልዮን ዩውሮ አፋጣኝ ርዳታ መስጠቱ የሚታወስ ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.