2009-04-16 11:22:16

ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የአብሩዞ ክፍለ ሃገርን ጐበኙ


በጣልያን ቤተክርስትያን የረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር እና የጀኖቫ ከተማ ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በመካከለኛው ጣልያን ባለፈው ቅርብ ግዜ በመሬት ነውጥ የተመታው አብሩዞ ክፍለ ሀገር መጐብኘታቸው ተገልጠዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በላአኲላ ከተማ በመሬት ነውጡ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው፣ በግዝያዊ መጠለያ ተንዳዎች የሚኖሩ ሰዎች፣ እየተዘዋወሩ መጐብኘታቸው እና በዚሁ ግዝያዊ መጠለያ፣ መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸውም ተመልክተዋል።

ከላአኲላ የደረሰ ዜና እንደሚያመልክተው፣ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር ሁለት ሚልዮን ዩውሮ ለአስቸኳይ እርዳታ ሰጥተዋል። ባለፈው ቅርብ ግዜ ረኪበ ጳጳሳቱ በመሬት መናወጥ ለተመታ አከባቢ፣ ለአፋጣኝ እርዳታ የሰጠው ሶስት ሚልዮን ኤውሮ ተጨማሪ ነው።

የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ለአብሩዞ ከሰጠው አምስት ሚልዮን ዩውሮ አስቸኳይ እርዳታ ባሻገር የሀገሪቱ ቤተክርስትያን የእርዳታ ተቋሞች የተለያዩ እርዳታዎች በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ የጣልያን ጳጳሳትን ወክለው አብሩዞ ክፍለ ሀገር እየጐበኙ መሆናቸውን ጠቅሰው የጣልያን ቤተክርስትያን ለአደጋ ከተጋለጠ የአብሩዞ ህዝብ ጐን እንደምትቆም እና በዳግመ ግንባታም አቅምዋ በፈቀደው ተሳታፊ እንድምትሆን አስታውቀዋል።

ሚያዝያ ስድስት ቀን አብሩዞ ላይ በተከሰተው የመሬት ነውጥ ሳቢያ 294 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ ከአንድ ሺ በላይ ከባድ እና ቀላል መቁሰልት እንደደረሰባቸው 55 ሺ መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው።

የዚሁ አደጋ ሰለባ የሆኑት ሰዎች የቀብር ስርአት ባለፈው ዓርብ በብዙ ሺ የሚገመት ህዝብ በተገኘበት መፈጸሙ የሚታወስ ነው።

መካከለኛው ጣልያን አብሩዞ ክፍለ ሀገር ለመሬት ነውጥ የተጋለጠ አከባቢ መሆኑ እና ዳግመ ግንባታው በየመሬት ነውጥ የማይደረመስ አግባብ ባለው አኳኀን ለማነጽ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጠዋል ።

በዳግመ ግንባታ ግዜ የኤውሮጳ ሕብረት አገሮች መሀንዲሶች ከጣልያን ጋር እንደሚተባበሩም ተያይዞ ተገልጠዋል።

በዚሁ አብሩጾ ክፍለ ሀገር አቨጻኖ ከተማ ላይ እኤአ በ1915 በደረሰው የመሬት ነውጥ 30 ሺ ህዝብ መሞቱ ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.