2009-04-15 18:51:20

የጣልያን ደናግል ሀገራዊ ማኅበር የበላይ ሐላፊዎች ጉባኤ


የጣልያን ደናግል ሀገራዊ ማኅበር የበላይ ሐላፊዎች ሮማ ላይ በሚገኘው ኡርባንያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ 56ኛ አመታዊ ጉባኤ መጀመራቸው ተነግረዋል።

የመነኲስያት ገዳማት የበላይ ሐላፊዎች ቃለ-እግዚአብሔር እና የሴቶች መንፈሳዊ ሕይወት ትኵረት የሰጠ ርእሰ ጉዳይ እንደሚመለከቱ ተገልጠዋል።

ሕይወታቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጡ መነኲስያት በማኅበራዊ ሕይወት ያላቸው ሚና በተመለከተም በዚሁ ኡርባንያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተጀመረው ጉባኤ ይወያይበታል።

ከዚሁ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የመጣ ዜና እንደገለጠው፣ ጉባኤው የጣልያን የመንኲስያት ገዳማት እና ማኅበራት እናቶች ባለንበት ወቅት ቃለ እግዚአብሔር እና አንደምታው፣ የቃለ እግዚአብሔር ገቢራውነት በተመለከተ ውይይት ይዘዋል።

እግዚአብሔርን ፈልጎ ማግኘት እና ይህን መንገድ ተከትሎ፣ ለሕይወት ኡውነተኛ ትርጉም መስጠት፣ ይህን ለዛሬ ወጣቶች መልእክት ማስተላለፍ በሚቻልበት ሁኔታ በኡርባንያን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የተሰበሰቡ እናቶች ውይይት መያዛቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.