2009-04-15 19:00:21

የላቲን ሥርዓት ትንሣኤ በኢራቅ


ኤስያ ኒውስ የተባለ የዜና አገልግሎት እንዳመልከተው፣ ዒራቅ ውስጥ ከበርካታ ግዝያት በኋላ ለመጀመርያ ግዜ የተረጋጋ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ተከብረዋል።

በተለያዩ ቁምስናዎች አከባቢ የሚገኙ ምእመናን የበዓለ ትንሣኤው መስዋዕተ ቅዳሴ ተሳታፊ ሁነዋል በማለት የዜና አገልግሎቱ አመልክተዋል።

ባለፈው የላቲን ሥርዓት ጸሎተ-ሐሙስ የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ሳዳም ሑሴን መንግሥታቸው የወደቀበት ዝክረ አመት በመኖሩ ባቅዳድ ውስጥ፣ ህውከት እና ግርግር የታከለበት ዕለት መኖሩ፣ የዜና አገልግሎቱ አስታውሶ፣ የካልደይ ፓትርያርክ ብፁዕ ኣቡነ ዘ/ባቢሎን ኤማኑኤል ሶስተኛ ደሊ ምእመናን ፍርሀት እንዲያወግዱ እና በፖሊስ እምነት እንዲያሳድሩ ማሳሰባቸው አስገንዝበዋል።

በዚሁ ዜና አገልግሎት መሰረት፣ ህውከት እና ግድያ በሰፈነባት ሞሱል ከተማ በመቶ ሰማንያ ክርስትያን ምእምናን የትንሣኤ በዓል ለማክበር ችለዋል።

ባሶራ ከተማ ላይም ካቶሊካውያን ፕሮተስታንቶች እና ኦርቶዶክሳውያን ከዕለተ ፋሲካ በፊት ተገናኝተው የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ ሐሳብ መለዋወጣቸውም ተያይዞ ተነግረዋል።

የወቅቱ የዒራቅ መንግሥት ፕረሲዳንት ጣላባኒ ለየዒራቅ ክርስትያን እንኳን ለትንሣኤ ደህና አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው ለሁለት ሺ አመታት ሀገሪቱ ውስጥ ላካሄዱት ሁለንትናዊ ስራ ማመስገናቸው ኤስያ ኒውስ ገልጠዋል።

ፕረሲዳንት ጣላባኒ የዒራቅ ክርስትያኖች ሀገሪቱ ውስጥ የሚያሳዩት የመቻቻል እና የወንድማማችነት መርሆዎች አመስግነው ዒራቅ ውስጥ ሰላም እና ፍትህ እንዲኖር እና እንዲጠናከር እንደሚረዳ መግለጣቸው ዜናው አስገንዝበዋል።

የሰው መሰረታዊ መብቶች የሚከበርባት እና ዲሞክርስያዊት ዒራቅ ለመመስረት የሚካሄደው ጥረት ቀጣይ መሆኑም ፕረሲዳንት ጣላባኒ መግለጣቸው ታውቆዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.